About Us

Welcome to Addis Ababa City Administration Code Enforcement Authority

In relation to the enforcement of rules, the city administration provides awareness to the public through various methods regarding the rules, controls and measures taken by the city administration.

Video Intro About the Authority
image description

A Brief History of Code Enforcement Authority

  • image description

    የደንብ ማስከበር ባለስልጣን አመሰራረት አጭር ገለፃ

    የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከር ባለስልጣን ከ2003 አስከ 2005 ዓ.ም በከተማዋ የሚስተዋሉ የደንብ መተላለፎችን ለመቀነስ እንዲቻል በቀድሞ በከተማ አስተዳደሩ ስራ አስኪያጅ ስር ማዘጋጃቤታዊ ተግራትን መሰረት በማድረግ በቡድን እና የተለያዩ የስራ ክፍል ስያሜዎች እየተሰጠው የደንብ ማስከበር ስራዎችን የሚያከናውን የስራ ክፍል የነበረ ሲሆን በወቅቱ የነበረው አደረጃጀት ከተማዋ ከምትፈልገው ውጤት እና ከታሰበለት ዓላማ ጋር የሚጋጭ አሰራር በመፈጠሩ ምክንያት በከተማ አስተዳደሩ ምክር ቤት እንዲፈርስ የተደረገ ቢሆንም ነገር ግን ተቋሙ በአሰራር እና በአደረጃጀት ተሻሽሎ መደራጀት እንዳለበት በመታመኑ በድጋሚ በከተማው ምክር ቤት በአዋጅ ቁጥር 37/2005 እና በደንብ ቁጥር 54/2005 ዝርዝር  ሃላፊነትና ተግባር ተሰጥቶት ራሱን የተቻለ ከማዕከል አስከ ወረዳ ድረስ መዋቅራዊ አደረጃጀትን በመያዝ የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር አገልግሎት ጽ/ቤት በሚል መጠሪያ ለከንቲባ ጽ/ቤት ተጠሪ ሆኖ የተመሰረተ ሲሆን ተቋሙ ከተመሰረተበት ጊዜ ጀምሮ በከተማው ውስጥ የሚፈፀሙ ደንብ መተላለፍ እና ተያያዥ ህገወጥ ተግባራትን ለመከላከል ለመቆጣጠር የሚያስችሉ የህግ ማዕቀፎችን በማዘጋጀት እንዲሁም በአሰራር ወቅት የሚገጥሙ ግድፈቶችን ለማረም የሚያስችሉ መመሪያዎች በመዘጋጀት እና በአዋጅ በተሰጠው ስልጣን እና ተግባር መሰረት ከነዋሪው ህብረተሰብ የተውጣጡ የደንብ መተላለፍ ክትትል፤ቁጥጥር እና እርምጃ አወሳሰድ ኦፊሰሮችን በመመልመል እና በህብረተሰቡ በማስተቸት ለመጀመሪያ ጊዜ በጦላይ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ተቋም ለ45 ቀናት የንድፈ ሀሳብ እና ወታደራዊ ስልጠና እንዲወስዱ በማድረግ ከግንቦት 1/2005 ዓ.ም ጀምሮ በሙሉ አቅም ወደ ተግባር መግባት ችሏል፡፡

    ሆኖም የከተማ አስተዳደሩ በአዋጅ ቁጥር 64/2011 አስፈፃሚ አካላትን እንደገና ለማቋቋም ባወጣው አዋጅ መሰረት ጽ/ቤቱን በሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ስር ዘርፍ ሆኖ እንዲቋቋም ተደርጎ እንዲሰራ የተደረገ ቢሆንም ይህ አደረጃጀት ተቋሙ የተሰጠውን ኃላፊነትና ተግባራትን ለማከናወን እንቅፋት የፈጠረ መሆኑ በወቅቱ ተገምግሞ  አደረጃጀቱ እንደገና እንዲቀየር ታምኖበታል፡፡ በመሆኑም ከተማ አስተዳደሩ አስፈጻሚ አካላትን ባቋቋመበት አዋጅ 74/2014 ዓ.ም በአንቀጽ 47 መሰረት ተጨማሪ ተግባርና ኃላፊነት ተሰጥቶት ባለስልጣን ሆኖ የተቋቋመ ሲሆን አዋጅ ቁጥር 74/2014 መሰረት በማድረግ ባለስልጣኑ ደንብ ቁጥር 150/2015 በም/ቤት በማጸደቅ እና መዋቅራዊ ክለሳ በማድረግ በአዲሱ አደረጃጀት መሰረት በሁለት ዘርፎች ማለትም የስልጠናና ቅድመ መከላከል እና የደንብ መተላለፍ ክትትል ቁጥጥር እና እርምጃ አወሳሰድ ዘርፍን በማደራጀት እንዲሁም በቀድሞ ከነበረው የአሰራር እና የአደረጃጀት ክፍተት መሰረት በማድረግ በአራተኛ ዙር የፓራሚሊተሪ ኦፊሰሮች ምልመላ እና የስልጠና ወቅት ለመጀመሪያ ጊዜ የደንብ መተላለፍ ቅድመ መከላከል ኦፊሰሮችን በማሰልጠን ባለስልጣኑ ከደንብ መተላለፍ ቁጥጥር እና እርምጃ ከመወሰዱ በፊት ስለ ደንብ መተላለፍ ምንነት፤ ህብረተሰቡ እና ተቋማት የመከላከል ሚናቸው እንዲሁም ድርጊቱ ተፈፅሞ ሲገኝ ሊያስከትሉ ስለሚችሉ የቅጣት መጠንን አስመልክቶ ግንዛቤ የሚፈጥሩ የቅድመ መከላከል ኦፊሰሮችን ወደ ስራ ማስገባት የቻለ ሲሆን አሁን ላይ ባለስልጣኑ ከአንደኛ አስከ አምስተኛ ዙር በሰጠው ስልጠና ቡቁ ሁነው የደንብ መተላለፍ ቅድመ መከላከል እና የደንብ መተላለፍ ክትትል ቁጥጥር እና እርምጃ አወሳሰድ ኦፊሰሮችን ቁጥር 6500 በላይ በማድረስ በከተማው ውስጥ የደንብ መተላለፍ ቀድሞ በመከላከል እና ድርጊቱም ተፈፅሞ ሲገኝ የቁጥጥር እና እርምጃ አወሳሰድ ተግባራትን የሚያከናውኑ የፓራሚሊተሪ ኦፊሰሮችን በከተማው ውስጥ በማሰማራት ውጤታማ ተግባራትን በማከናወን ላይ ያለ ሲሆን ባለስልጣኑ በአዋጁ የተሰጡትን ተግባር እና ኃላፊነትን በብቃት መፈፀም እንዲቻል ቀድሞ የነበሩ የህግ ማዕቀፎች ላይ የነበሩ የአሰራር ክፍተቶችን በመለየት በአሁኑ ጊዜ ከከተማ እድገት እና የነዋሪዎቿ ፍላጎት ጋር ተነፃፃሪ የሆነ ብሎም በአሰራር እና በአደረጃጀት ዘመኑን የዋጀ የደንብ ማስከበር አሰራሮችን በመቅረፅ በተሻለ ቁመና መደ ተግባር መግባት ችሏል፡፡

     

Structure Of The Authority

Vision

In 2022, the city of Addis Ababa saw a decrease in regulation as a convenience for its residents as well as a model for African cities. 

Mission

To make Addis Ababa City comfortable, attractive and peaceful for its residents by preventing, controlling and taking action against violations and related illegal activities through the inclusive participation of the community.

Values

1. Fight steadfastly for the rule of law,
2. Accountability, 
3. Participatory
4. Put the public interest above oneself,
5. Servitude 
6. Loyalty,
7. Standing up for a common cause