
ባለስልጣኑ በቀጣይ ለሚሰጠው የ6ኛ ዙር የፓራ-ሚሊተሪ ኦፊሰሮች ስልጠና በተመለከተ ከኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ጋር የስልጠና እቅድ ውይይት አደረገ ::
ባለስልጣኑ በቀጣይ ለሚሰጠው የ6ኛ ዙር የፓራ-ሚሊተሪ ኦፊሰሮች ስልጠና በተመለከተ ከኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ጋር የስልጠና እቅድ ውይይት አደረገ ::
የካቲት 6/2017
****የአዲስ አበባ****
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ከኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር በቀጣይ ለሚሰጠው ስድስተኛ ዙር የፓራሚሊተሪ ኦፊሰሮች ስልጠና ስርአተ ትምህርት እና አጠቃላይ የስልጠና ሂደቱን እቅድ ላይ የሁለቱ ተቋማት ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ውይይት አድርጓል::
ስልጠና በንድፈ ሀሳብ እና በአካል ብቃት የጎለበተ ህጉን ከቃል በበለጠ መሬት ላይ ማስከበር የሚችል ኦፊሰር ከማፍራት አንፃር ጉልህ ሚና አለው ያሉት የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ በስልጠናው ዘርፈ ብዙ ልምድ ካለው ተቋም ጋር መስራታችን በንድፈ ሀሳብና በአካል ብቃትም የጎለበተ የሰው ሀይል ለመገንባት ጉልህ ሚና አለው ብለዋል::
አጠቃላይ የስልጠና ሂደቱን በሚመለከት ስርአተ ትምህርቱን እና አጠቃላይ የበጀት እቅድ ሰነድ በስልጠናና ጥናት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በወ/ሮ ላቀች ሃይሌ የቀረበ ሲሆን በሰነዱም ስለ ስልጠናው አላማ፣ የጊዜ ሰሌዳ፣ የሰው ሀይል ትንተና፣ስለ ትምህርት እና ፈተና አሰጣጥና የምዘና ሂደት እንዲሁም የግብአት እና በጀት ጉዳዮች ቀርበው ውይይት ተደርጓል::
የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ም/ጀነራል መስፍን አበበ በመጡት አመራሮች በእውቀት እና በአካል የዳበረ የሰው ሀይልን ይዞ እንደተቋም ለመራመድ ታስቦ ይህ ስልጠና መዘጋጀቱ መልካም መሆኑ ገልጸው ይህ እቅድ እንዲሳካ ዩኒቨርሲቲው የበኩሉን እንደሚወጣ ገልጸዋል ::
በመጨረሻም ከቤቱ የተነሱትን ሀሳብ እና አስተያየቶች የጋራ በማድረግ ወደ ትግበራ እንደሚገባ በመግለጽ ውይይቱ ተጠናቋል::
ዘገባው :- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ነው፡፡
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments