
ባለስልጣኑ የወርቃማ ሰኞ ማለዳ የሰራተኞች የእውቀት ሽግግር መርሃ ግብር አከናወነ።
ባለስልጣኑ የወርቃማ ሰኞ ማለዳ የሰራተኞች የእውቀት ሽግግር መርሃ ግብር አከናወነ።
10 -06 -2017 ዓ.ም
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ሰኞ ማለዳ ከስራ ገበታ በፊት የሚያካሂደው የእውቀት ሽግግር ፕሮግራም የባለስልጣኑ አመራሮች እና ሰራተኞች በተገኙበት አካሄደ፡፡
የመድረኩ ንግግር ያደረጉት የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ 38 የአፍሪካ ህብረት ስብሰባ ያለምንም የጸጥታ ችግር እንዲጠናቀቅ ከአመራሩ ጀምሮ እስከ ኦፊሰሩ የተሰጠውን ተልዕኮ በአግባሙ መወጣትና መፈጸም ችሏል ለዚህም ለሰራው መሳካት አስተዋጽኦ ላደረኩ አካላት ምስጋናቸውን በማቅረብ መጪው ሳምንት ስራዎቻችን በአግባቡ የምንወጣበት የደስታ ሳምንት እንዲሆን መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል ።
በዕለቱ የባለስልጣኑ የስታንዳርዳይዜሽን ዝግጅት፣ አገልግሎት አሰጣጥድጋፍ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ዳንኤል ቀጸላ የራሳቸውን የህይወትና የትምህርት እና የስራ ተሞክሮና ልምዳቸውን ለሌሎች አስተማሪ በሆነ መልኩ አጋርተዋል።
ባለስልጣኑ ሁልጊዜ አዳዲስ ሀሳቦችን ፣ተግባራትን ለማወቅ በሞመከር ጥረት ውስጥ ማለፍ ዉጤታማና ስኬታማ እንደሚያደርግ ገልጸዋል ፡፡
በተጨማሪም በመድረኩ የተቀናጀ የሲቪል ሰርቪስ መረጃ አያያዝ ስርዓት" (ICSMIS ) ሲስተሙን የመጠቀሚያ ስም እና ማለፊያ ቃል በማዘጋጀት የዓመት እረፍትና የስራ ልምድ በሲስተም የሚጠየቅ መንገድ መመቻቸቱን የሰው ሀብት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን ይልማ ገልጸዋል
ዘገበው ፡-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳሬክቶሬት ነው፡፡
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments