የደንብ ማስከበር ተግባርን ወደ መሬት ለማዉረድ...

image description
- In code inforcement    0

የደንብ ማስከበር ተግባርን ወደ መሬት ለማዉረድ ኦፊሰሩን በስነ-ምግባር ማነጽ ይገባል ተባለ

የደንብ ማስከበር ተግባርን ወደ መሬት ለማዉረድ   ኦፊሰሩን በስነ-ምግባር ማነጽ ይገባል ተባለ

         11/06/2017 ዓ.ም
        ****አዲስ አበባ****

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ህገወጥ ተግባር የመከላከል፣ የመቆጣጠር እና እርምጃ የመዉሰድ ተልዕኮውን ለመወጣት በስነ-ምግባር ኦፊሰርን ለማብቃት የሚያስችል ስልጠና በየካ ክፍለ ከተማ አዳራሽ አካሄደ።

በስልጠናው ላይ የክፍለ ከተማው ወረዳ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት ኃላፊዎች፣ የክፍለ ከተማው የስነ-ምግባርና ፀረ ሙስና ቡድን መሪ፣ ተባባሪ አካላትና አጠቃላይ ኦፊሰሮች ተገኝተዋል።

በእለቱ ስልጠናውን የሰጡት የባለስልጣኑ የስነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ዳይሬክተር አቶ እዮብ ከበደ ብልሹ አሠራርን ከመልካም አስተዳደር አኳያ በማየት የአገልግሎት አሰጣጥን በማዘመን ለችግሩ መፍትሔ ማስቀመጥ የስልጠናው ዓላማ ነው ሲሉ ገልጸዋል።

በመሆኑም ባለስልጣኑ ኦፊሰሩን ከብልሹ አሠራር እራሱን በመጠበቅ የተሰጠዉን ተልዕኮ ከዳር እንዲያደርስ የተለያዩ የአቅም ግንባታ ስልጠናዎች እየሠጠ እንደሚገኝና በቀጣይም ክፍተት የታየባቸውን ቦታዎች ላይ ትኩረት በማድረግ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ተገልጽዋል።

በውይይቱም ላይ ከመዋቅር ጋር በተያያዘ ፣ የደመወዝ ልዩነት እና ሌሎች ጥቅማ ጥቅም በሚመለከት የተለያዪ ጥያቄዎች በውይይቱ ተነስቷል። 

ኦፊሰሩ ከህዝቡ ወቶ ሠልጥኖ መልሶ ህብረተሰቡን  የሚያገለግል እንደመሆኑ ሁልጊዜ እራሱን ከብልሹ አሠራር የጸዳ ህብረተሰቡን በታማኝነት  የሚያገለግል ሊሆን ይገባል በሚል በውይይቱ ለተነሱት ጥያቄዎችና አስተያየቶች ከመድረኩ ምላሽ ተሰጥቷል።

በመጨረሻም የክፍለ ከተማው ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አያልነህ ሙላቱ በማጠቃለያዉ ላይ ባስተላለፋት መልክት እንደ ከተማም ሆነ ክፍለ ከተማ ያለውን ኢኮኖሚያዊ ፣ ፖለቲካዊ እና ማህበራዊ ስራዎች የተሳለጠ እንዲሆን የደንብ ማስከበር ኦፊሰሩ ከስልጠናዉ ያገኘውን እውቀት ወደ ተግባር በመለወጥ እራሱን በስነ-ምግባር እና መልካም አስተዳደር በማነጽ የአገልግሎት አሰጣጡን በማሻሻል ተልዕኮውን እንዲወጣ አሳስበዋል።

ዘገባው:- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኔኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ነው።፥


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments