ባለስልጣኑ ተልዕኮውን ለመወጣት በስነ-ምግባር ኦ...

image description
- In code inforcement    0

ባለስልጣኑ ተልዕኮውን ለመወጣት በስነ-ምግባር ኦፊሰርን ለማብቃት እየሰራ እንደሚገኝ ተገለጸ።

ባለስልጣኑ ተልዕኮውን ለመወጣት በስነ-ምግባር ኦፊሰርን ለማብቃት እየሰራ እንደሚገኝ ተገለጸ።

                 11/06/2017 ዓ.ም
                    ****አዲስ አበባ****

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ህገወጥ ተግባር ለመከላከል፣ ለመቆጣጠር እና እርምጃ ለመውሰድ የተጣለበትን አላማ ለመወጣት በስነ-ምግባር ኦፊሰርን ብቁ ለማድረግ የሚያስችል ስልጠና በቦሌ ክፍለ ከተማ አዳራሽ አካሄደ።

 "ስነ-ምግባር እና መልካም አስተዳደር ለተሻለ አገልግሎት" በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀውን  ስልጠና የሰጡት የባለስልጣኑ የስነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ዳይሬክተር አቶ እዮብ ከበደ ሲሆኑ ብልሹ አሠራርን ከመከላከል እና ለችግሩ መፍትሔ ከማስቀመጥ አኳያ የኦፊሰሩን ግንዛቤ ማጠናከር  የስልጠናው ዓላማ ነው ሲሉ ገልጸዋል።

በቀረበው ሰነድ ላይ በመነሳት ከቤቱ ከሞያ ስነምግባር እና ለስራው ክብር ከመስጠት አንጻር ስልጠናው ክፍተታችንን ይሞላል ያሉት ተሳታፊዎች በቀጣይም ሰፋ ያለ የጊዜ ሰሌዳ ተዘጋጅቶ ህብረተሰቡን የማንቃት ግንዛቤ የመፍጠር ስራ ቢሰራ የሚሉ እና ሌሎች የተለያዪ ጥያቄዎች እና አስተየቶች ተነስተዋል። 

ኦፊሰሩ ከማህበረሰቡ ወጥቶ ህብረተሰቡን  የሚያገለግል እንደመሆኑ ሁልጊዜ የተለያዩ ችግሮች ቢገጥመውም ቢነሳበትም እራሱን ከብልሹ አሠራር በማራቅ ህብረተሰቡን ህጉ በሚለው መሰረት የሚያገለግል ሊሆን ይገባል በሚል በውይይቱ ለተነሱት ጥያቄዎችና አስተያየቶች ከመድረኩ ምላሽ ተሰጥቷል።

በመጨረሻም የክፍለ ከተማው ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት ኃላፊ ኮ/ር አስፋው የሺዳኜ በማጠቃለያዉ ላይ ባስተላለፋት መልክት እንደ ክፍለ ከተማ ያለውን ህብረተሰብን የማገልገል ስራዎች የተቀላጠፈ እንዲሆን ኦፊሰሩ ከስልጠናዉ ባገኘው እውቀት የተሻለ ስራ መስራት እንዲችል እና እራሱን በስነ-ምግባር በማነጽ ኃላፊነቱን እንዲወጣ አሳስበዋል።

ዘገባው:- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኔኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ነው።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments