
ባለስልጣኑ የስድስተኛ ዙር የኦፊሰር የምልመላ ሂደት በተመለከተ ውይይት አካሄደ
ባለስልጣኑ የስድስተኛ ዙር የኦፊሰር የምልመላ ሂደት በተመለከተ ውይይት አካሄደ
11-06 -2017 ዓ.ም
****አዲስ አበባ****
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የስድስተኛ ዙር የኦፊሰር ምልመላ ሂደት እና የነባር ኦፊሰሮች ምደባ ዙሪያ የባለስልጣኑ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ከክፍለ ከተማ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት ኃላፊዎች ጋር ውይይት ተካሄደ ።
በመድረኩ ንግግር ያደረጉት የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ ለተቋሙ ህገ-ወጥነትና ብልሹ አሰራርን የሚጸየፍ ፤የከተማውን ደህንነት የሚያስጠብቅና ለስራዎች መሳካት ዝግጁ የሆነ አባል ስለሚያስፈልገው የምልመላ መስፈርቱን መሠረት በማድረግ የሚያሞሉ ወጣቶችን ብቻ መመዝገብ እንዳለበት ገልጸዋል ።
የባለስልጣኑ ም/ስራ አስኪያጅ አቶ ከፍያለው ታደሰ በበኩላቸው እንደተናገሩት የሚመዘገቡት ምልምል ኦፊሰሮች የወጣውን የዕድሜ ፣ የትምህርት ማስረጃ ፣ የአቋም፣ የስነምግባርና የመሳሰሉት መስፈርቶችን የሚያሟሉትን ጥርት ባለ መልኩ ምልመላ ማካሄድ ይገባናል ሲሉ ገልጸዋል ።
በውይይቱ መድረኩ የስድስተኛ ዙር የኦፊሰር ምልመላ ምዝገባ ሂደት አሁናዊ ሪፖርት የተመረጡ ክፍለ ከተሞች አቅርበው
የሰልጣኞች ምልመላም የተሳለጠ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስቸል በመሆኑ በተሰጠው አቅጣጫ መሰረት ምዝገባው መጀመራቸውና መስፈርቱን የሚያሟሉ ሰልጣኞች በወረዳዎች እየተመዘገቡ እንደሚገኙ የክ/ከተማ ኃላፊዎች ገልጸዋል ፡፡
የባለስልጣኑ ም/ስራ አስኪያጅ አቶ ንጋቱ ዳኛቸው ስነ-ምግባር የተላበሰና የሰላም ሀይል ለከተማው ሆኖ የሚያገለግል የኦፊሰር ምልመላ ለማድረግ ወደ ህብረተሰቡ ተደራሽ ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል ።
አክለውም ከአደረጃጀት አመራርና ከፖለቲካ አመራር ጋር የምልመላ ሁኔታውን የጋራ ማድረግ አስፈላጊ ነው ብለዋል።
በመድረኩ የኦፊሰሩን ሁኔታ ያገናዘበ የስራ መደብ ሁኔታ በማዘጋጀት ጥናት ተጠናቆ ወደ ተግባር መገባቱ ገልጸው ምደባው በጥንቃቄና በመመሪያው መሠረት መከናወን እንዳለበት የባለስልጣኑ የሰው ሀብት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን ይልማ ተናግረዋል ።
በመጨረሻም በውይይቱ ለተነሱ ሀሳብና ጥያቄዎች በባለስልጣኑ ከፍተኛ አመራሮች ምላሽ ተሰጥቶበታል ።
ዘገበው ፡-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳሬክቶሬት ነው፡፡
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments