ባለስልጣጣኑ "ሰው ተኮር ተግባሮቻችን ለአብሮነታ...

image description
- In code inforcement    0

ባለስልጣጣኑ "ሰው ተኮር ተግባሮቻችን ለአብሮነታችን" በሚል መሪ ቃል የአቅመ ደካማ እናት ቤት እድሳት አጠናቆ ለባለቤቱ የቁልፍ ርክክብ አደረገ

ባለስልጣጣኑ "ሰው ተኮር ተግባሮቻችን ለአብሮነታችን"  በሚል መሪ ቃል የአቅመ ደካማ እናት ቤት እድሳት አጠናቆ  ለባለቤቱ የቁልፍ ርክክብ አደረገ

             13/06/2017 ዓ.ም
                አዲስ አበባ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን  በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤቱ "ሰው ተኮር ተግባሮቻችን ለአብሮነታችን" በሚል መሪ ቃል በወረዳ 02 ለሚገኙ አቅመ ደካማ የመኖሪያ ቤት ገንብቶ በማጠናቀቅ ለባለቤቶቹ አስረከበ፡፡

በቤቱ ምርቃት መርሀ-ግብር ላይ የአዲስ አበባ የደንብ ማስከበር ባለ ስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን  የክፍለ ከተማው ደንብ ማስከበር ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ሙሉጌታ ጎንፋ ፣የወረዳ ደንብ ማስከበር አመራሮችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡

በፕሮግራሙ የተገኙት የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ ተቋሙ ደንብ መተላለፎችንና ህገ-ወጥ ተግባራትን ከመከላከል ጎን ለጎን ወደ ማህበረሰቡ በመውረድ ሰው ተኮር የበጎፍቃድ ስራዎችን በመስራት ለህብረተሰቡ ያለውን አለኝታነት በተግባር እያሳየ ይገኛል ይህ  ሰው ተኮር በጎ ተግባር በቀጣይም ተጠናክሮ  እንደሚቀጥል ተናግረዋል።

በምርቃት ፕሮግራሙ የኮልፌ ክፍለ ከተማ ደንብ ማስከበር ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ሙሉጌታ ጎንፋ በኑሮአቸው ዝቅተኛ ገቢ ላላቸውና ረዳት ለሌላቸው የማህበረሰብ ክፍሎች በሰው ተኮር ተግባራት ላይ በመሳተፍ በክ/ከተማው በቤት እድሳት፣ማእድ በማጋራትና በሌሎች የተለያዩ ሰው ተኮር ስራዎች እያከናወነ ይገኛል ብለዋል፡፡

አክለውም የብልፅግና እሳቤ ከሆነው የሰው ተኮር ስራ አንዱ በዛሬው እለት በክፍለ ከተማው ያሉ ወረዳዎችን በማስተባበር  የአቅመ ደካማ ቤት እድሳት በማጠናቀቅ ለባለቤቱ አስረክበዋል በቤት እድሳት ወቅት አስተዋጾ ላበረከቱ አካላት ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

የቤት እድሳት የተደረገላት የወረዳ ነዋሪ የሆኑት ወ/ሮ ሙሪዳ አወል ከደንብ ማስከበር አመራርና አባላት ለተደረገላቸው ድጋፍ ከልብ አመስግነዋል፡፡

ዘገበው ፡-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳሬክቶሬት ነው፡፡


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments