የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት በ...

image description
- In code inforcement    0

የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት በደንብ ቁጥር 180/2017 ላይ ግንዛቤ ፈጠረ

የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት በደንብ ቁጥር 180/2017 ላይ ግንዛቤ ፈጠረ

                  የካቲት 14/2017 ዓ.ም
                ****አዲስ አበባ***

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቂርቆስ ክ/ከተማ ደንብ ማስከበር ፅ/ቤት ከክፍለ ከተማው ፍትህ ጽ/ቤት ጋር በመተባበር በደንብ ቁጥር 180/2017 እና በተለያዩ የህግ ማእቀፎች ላይ ለክ/ከተማ እና ለወረዳ አመራሮች እና የማኔጅመንት አባላቱ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ አካሄደ።

በመድረኩ የክ/ከተማው ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዳኜ ሂርጳሳ በደንብ ቁጥር 180/2017 እና በተለያዩ የህግ ማእቀፎች ላይ ግንዛቤ ለመፍጠር እና ኦፊሰሩ ህገወጥ ተግባራትን በመከላከል ሂደቱ ላይ ለሚያጋጥሙ የህግ ክፍተቶች ለማረቅ እና ጥያቄዎች ለመመለስ እንዲቻል መድረኩ መዘጋጀቱ ገልጸዋል።

የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኩም የክፍለ ከተማው ፍትህ ጽ/ቤት አቃቤ ህግ ዮናስ ጎዳና በደንብ ቁጥር 180/2017 እና በተለያዩ የህግ ማእቀፎች ላይ ሰነድ ከሰፊ ማብራሪያዎች ቀርቧል።

በእለቱ ከተለያዩ ተሳታፊ አካላት ጋር ደንቡን ተግባራዊ ለማድረግ ግልጽ ባልሆኑ ጉዳዮች ላይ ጥያቄ እና አስተያየቶች በማንሳት ውይይት ተካሂዷል።

በመጨረሻም የክ/ከተማው ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዳኜ ሂርጳሳ ባስተላለፋት መልዕክት ከመድረኩ ያገኛችሁትን ግንዛቤዎች በንባብ በመደገፍ ወደ ተግባር መቀየር እንደሚገባ በመግለጽ በትግበራዉ ወቅት ለሚያጋጥሙ ችግሮችም ሆኑ ማንኛውም ጥያቄዎች ከፍትህ ጽ/ቤት ጋር በጋራ በመሆን መስራት እንደሚገባ አሳስበዋል።

ዘገባው:- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኔኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ነው።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments