አራዳ ክ/ከተማ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት በኮሪደር...

image description
- In code inforcement    0

አራዳ ክ/ከተማ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት በኮሪደርና የፀጥታ ስራዎች አፈጻጸም የእውቅና የሽልማት መርሃ ግብር አካሄደ

አራዳ ክ/ከተማ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት በኮሪደርና የፀጥታ ስራዎች አፈጻጸም የእውቅና የሽልማት መርሃ ግብር አካሄደ

        የካቲት 16/2017 ዓ.ም
         ****አዲስ አባባ**** 

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በአራዳ ክ/ከተማ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤቱ በኮሪደር ልማት፣በፀጥታ ስራዎች እና በ2017 በጀት አመት የ6 ወር እቅድ አፈጻጸም ከፍተኛ አስተዋፅኦ ላበረከቱ አካላት የእውቅናና ሽልማት መርሃ ግብር አካሂዷል።

በመድረኩ የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ፣ የባለስልጣኑ ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ ንጋቱ ዳኛቸው፣ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ ምክትል ሀላፊ አቶ ሚደቅሳ ከበደ ፣የአራዳ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ጌታሁን አበራ፣ሌሎች የክ/ከተማው  ጽ/ቤት ሀላፊዎች፣የመከላከያ፣ የፌደራል እና የከተማው የፖሊስ አባላት፣ ባለድርሻ አካላት ፣ የወረዳ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት ኃላፊዎች ፣ ኦፊሰሮች፣ የሀገር ሽማግሌዎች ፣ የሀይማኖት አባቶች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል ።

በመድረኩ የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ ዓለምን ያስደመመው አፍሪካውያንን ያነጋገረ የአዲስ አበባ የልማት ስራ ላይ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላበረከቱ አባሎቻችን እና ባለድርሻ አካሎች ከልብ አመስግነው  የመጀመሪያ የኮሪደር ልማት ስረሠ የተጀመረው በአራዳ ክፍለ ከተማ ላይ ነው የአራዳ ክፍለ ከተማ ነው ለዚህም ትልቁ ኃይላችን የደንብ ማስከበር እንደነበር ገልጸዋል።

በዚህም ኦፊሰሩ ለልማት የተነሱ እናቶቻችን እና አባቶቻችን ያለምንም ወጪ እቃቸውን ወደ ተሽከርካሪ በመጫንና ወደ ተሰጣቸውም ቦታ  በመውሰድ  የአራዳ ክፍለ ከተማ ኦፊሰሮችና አመራሮች ከፍተኛ ሚና መጫወታቸው ጠቁመዋል።

የመድረኩ ንግግር ያደረጉት የአራዳ ክ/ከተማ  ጽ/ቤቱ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ጌታሁን አበራ ደንብ ማስከበር በየጊዜው እያደገና እየተሻሻለ የሚገኝ ተቋም መሆኑና እያከናወናቸው ያሉ ውጤታማ ተግባራት በግልጽ ማሳያ ናቸው በማለት በቀጣይ ተቋሙ ለሚያከናውኗቸው ስራዎች ከጎኑ ሆነው እንደሚደግፉ ተናግረዋል ።

የአራዳ ክ/ከተማ ሰላምና ፀጥታ ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ አብዲ የተሰራው የኮሪደር ልማት ስራው ተውቦና ደምቆ የምናየው ከፊትም ከኋላም ደንብ ማስከበር አባላት መሰዋዕትነት እየከፈሉ ደህንነቱ ተጠብቆ እንዲቆይ ላደረጉት አስተዋፅኦ ተቋሙና አባላቱ ማመሰገን፣ ማክበር እና መሸለም እንደሚገባ ገልፀዋል።

በመድረኩ የእንኳን ደና መጣቹ ንግግር ያደረጉት የአራዳ ክ/ከተማ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት ሀላፊ ሻምበል ኑርልኝ ገ/ኪዳን ቀን እና ሌሊት የሰሩ የደንብ ማስከበር ተልዕኮ ተቀብለው  የሚታዩ የደም መተላለፍና ህገ-ወጥ ተግባራትን በመቆጣጠር በመከላከል በዚህ ስድስት ወር ውስጥ የደንብ  የደንብ መተላለፍ 53.9% መቀነሱ ገልጸዋል።

አክለውም እውቅና እና ሸልማት መሠጠቱ የተሰሩ ስራዎችን ከባለድርሻ አካላትና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቀጣይ ለሚከናወኑ ተግባራት የተሻለ አፈጻጸም ለማምጣት ጉልህ ሚና አንዳለው ገልጸው ከ1ኛ - 3ኛ የወጡ ወረዳዎች እውቅና እና ሸልማት ተበርክቶላቸዋል።

እውቅና እና ሸልማት በአፈፃፀማቸው መሠረት 1ኛ ወረዳ 5 ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት
2ኛ ወረዳ 6 ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት
3ኛ ወረዳ 9 ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት በመውጣት እውቅና እና ሸልማት ተበርክቶላቸዋል።

ዘገበው ፦ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments