
በቴክኖሎጂ የታገዘ ስራዎችን ለማከናወን የአቅም ግንባታ ስልጠና እየተሰጠ ነው።
በቴክኖሎጂ የታገዘ ስራዎችን ለማከናወን የአቅም ግንባታ ስልጠና እየተሰጠ ነው።
18/06/2017 ዓ.ም
****አዲስ አበባ *****
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ከኢኖቬሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ ጋር በመተባበር ለባለስልጣኑ የማዕከል ሰራተኞች የመስክ ማስተዳደር ስርዓት/ Field managements system/ በሚል የስልጠና ርዕሰ የሚሰጠው ስልጠና ሜክሲኮ በሚገኘው በተግባረዕድ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ መሰጠት ጀመረ።
ስልጠናውን ያስጀመሩት የባለስልጣኑ የስልጠና ዳይሬክተር ወ/ሮ ላቀች ሀይሌ በስልጠናው ማስጀመሪያ ላይ በመገኘት ስራዎችን በቴክኖሎጂ ለማሳለጥ የቴክኖሎጂ አጠቃቀም ዕውቀት መገንባት ወሳኝ ስለሆን ስልጠናው ይህንን ክፍተት የሚሞላ መሆኑን ገልፀዋል።
ስልጠናዉ ከኢኖቬሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ በመጡ በአቶ ሀብታሙ ጴጥሮስ Field mangement system (FMS) እና በአቶ አማኑኤል መኮንን file mangement system (FMS) ዙሪያ ለሁለት ቀናት እንደሚሰጥ ተገልፆ በተግባር የታገዘ ስልጠና እንደሆነ አስታውቀዋል።
ዘገባው የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ነዉ።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments