የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት...

image description
- In code inforcement    0

የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት የ2017 በጀት ዓመት በ6 ወር የሥራ አፈፃፀም የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ አካላት እውቅና ሰጠ

የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት የ2017 በጀት ዓመት በ6 ወር የሥራ አፈፃፀም የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ አካላት እውቅና ሰጠ

           የካቲት 18-2017 ዓ.ም
          ****የአዲስ አበባ****

የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ደንብ ማስከበር አስተዳደር ጽ/ቤት የ2017 በጀት ዓመት በ6 ወር የሥራ አፈፃፀም የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ ተቋማት ፣ወረዳዎችና ፈፃሚዎች የእውቅና የምስጋና ፕሮግራም አካሄዷል፡፡ 

በበጀት ዓመቱ 6 ወራት ውስጥ ህገ ወጥ የመሬት ወረራ፣ ህገ ወጥ ንግድ፣ ያለ ፈቃድ ማስታወቂያ መለጠፍ፣ ህገ ወጥ እርድ እንዲሁም አዋኪ ድርጊቶችን ህግና አሰራር በጠበቀ መንገድ አስተማሪ እርምጃ በመወስድ የከተማዋን ብሎም የክ/ከተማችንን ህግና ስርዓትን በማስፈን የህብረተሰቡን በሁሉ አቀፍ የተረጋጋ እንቅስቃሴ እንዲኖር ማድረግ መቻሉን የጽ/ቤቱ ሃላፊ አቶ ደጀኔ ነጋሮ ገልፀዋል፡፡ 

በመድርኩ ተሳታፊዎች ሀሳብ አስተያየት እንዲሁም ጥያቄዎች አንስተው ከመድረክ መሪው በቂ ምላሽ ተሰቶበት በቀሩት ሥራዎች በቀጣይ የሚሰራ መሆኑን መግባባት ላይ ተደረሷል፡፡

በ6 ወር የሥራ አፈፃፀም የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ ወረዳዎች የእውቅና የተሰጠ ሲሆን በዚህም መሠረት፡-
1ኛ ወረዳ 1 ደንብ ማስከበር አስተዳደር ጽ/ቤት
2ኛ የወረዳ 4 ደንብ ማስከበር አስተዳደር ጽ/ቤት
3ኛ የወረዳ-10 ደንብ ማስከበር አስተዳደር ጽ/ቤት  በመወጣት ዋንጫና ሠርተፍኬት ተበርክቶላቸዋል፡፡


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments