
የወንዝ ዳርቻ ልማትን ከብክለት በሚከላከል ደንብ ቁጥር 180/2017 ላይ ግንዛቤ ሊሰጥ ነው።
ፕሬስ ሪሊዝ
የወንዝ ዳርቻ ልማትን ከብክለት በሚከላከል ደንብ ቁጥር 180/2017 ላይ ግንዛቤ ሊሰጥ ነው።
19/06/2017 ዓ.ም
****የአዲስ አበባ****
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ከአከባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ጋር በመተባበር "የወንዝ ዳርቻ ልማት እና ብክለት መከላከል" በሚል በወጣው ደንብ ቁጥር 180/2017 ላይ ነገ ሀሙስ በ20/06/2017 ዓ.ም ጉርድ ሾላ በሚገኘው አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ቢሮ ከጠዋቱ 2:30 ጀምሮ ግንዛቤ እንሚፈጠር የባለስልጣኑ ኮሙኔኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ የምስራች ግርማ አስታወቁ።
በግንዛቤ ስልጠናው ላይ የደንብ ማስከበር ባለስልጣን የቅድመ መከላከልና መስክ ክትትል፣ ቁጥጥር ኦፊሰሮች የባለስልጣኑ ባለሙያዎች፣ የከተማ ውበትና አረንጓዴ ልማት ቢሮ አመራሮችና ባለሙያዎች እንዲሁም ባለድርሻ አካላት የግንዛቤ ስልጠናው ተሳታፊዎች እንደሚሆኑ አቶ የምስራች ገልፀዋል።
በቀጣይም ለከተማው ህብረተሰብ፣ ለባለድርሻ አካላት፣ ለአደረጃጀቶችና በጎ ፈቃደኞች ስለ ደንቡ ግንዛቤዎች በስፋት እንደሚፈጠር ጠቁመዋል።
ጥቆማው ፦ የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ነው።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments