
ሙስናና ብልሹ አሰራሮችን ለመከላከል ስልታዊና ቅንጅታዊ አሰራሮችን ማጠናከር እንደሚገባ ተገለጸ
ሙስናና ብልሹ አሰራሮችን ለመከላከል ስልታዊና ቅንጅታዊ አሰራሮችን ማጠናከር እንደሚገባ ተገለጸ
የካቲት 19/2017 ዓ.ም
****አዲስ አባባ****
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ለጉለሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት ፓራ-ሚሊተሪ ኦፊሰሮች በስነ-ምግባር፣ ፀረ-ሙስና እና በመልካም አስተዳደር ዙሪያ ስልጠና ሰጠ።
በስልጠናው በሙስና መከላከል ስነ- ምግባራዊ አመራር፣ በጥቅም ግጭት እና አስቸኳይ ሙስና መከላከል ስልታዊና ቅንጅታዊ አሰራር ዙሪያ ሲሆን በፀረ-ሙስናና ብልሹ አሰራሮች የቀጣይ እቅዶችን ዙሪያ ማብራሪያ ተሰጥቷል።
ስልጠናውን የሰጡት የባለስልጣኑ የስነ-ምግባርና የፀረ ሙስና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ እዮብ ከበደ ተቋሙ በሰጠው ስልጠናና ግንዛቤ መሠረት በቀጣይ የስነ-ምግባር ችግር በሚታይባቸው ሰራተኞች ላይ የሚወስደውን እርምጃ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፀዋል።
በስልጠናው የጉለሌ ክፍለ ከተማ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት ኃላፊ ኮማንደር ግርማ ሰንበቶ እንደተናገሩት ኦፊሰሩን ከብልሹ አሠራር እራሱን በመጠበቅ የተሰጠዉን ተልዕኮ ከዳር ማድረስ እንዳለበት ገልጸዋል።
አክለውም ኦፊሰሩ ሙስናን በመከላከል በኩል ከፍተኛ ድርሻ እንዳላቸው በመግለጽ ኦፊሰሩ በሚሰጡ የአቅም ግንባታ ስልጠናዎች እውቀት በመጨመር ሙስናና ብልሹ አሰራሮችን ለመከላከል ስልታዊና ቅንጅታዊ አሰራሮችን ማጠናከር እንደሚገባ ገልፀዋል።
በስልጠናው ላይ የክፍለ ከተማውና የወረዳ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት ኃላፊዎች፣ የክፍለ ከተማው የስነ-ምግባርና ፀረ ሙስና ባለሙያ፣ ተባባሪ አካላትና አጠቃላይ ኦፊሰሮች ተገኝተዋል።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments