የወንዞች ዳርቻ ልማት እና ብክለት ለመከላከል በ...

image description
- In code inforcement    0

የወንዞች ዳርቻ ልማት እና ብክለት ለመከላከል በወጣዉ ደንብ ቁጥር 180/2017 ላይ ግንዛቤ ተፈጠረ።

የወንዞች ዳርቻ ልማት እና ብክለት ለመከላከል በወጣዉ ደንብ ቁጥር 180/2017 ላይ ግንዛቤ ተፈጠረ።

    20/06/2017 ዓ.ም
       ****አዲስ አበባ****

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአከባቢ ጥበቃ ባለስልጣን፣ የደንብ ማስከበር ባለስልጣን እና ከተማ ዉበትና አረንጓዴ ልማት ቢሮ በመተባበር
የወንዞች ዳርቻ ልማትን እና ብክለት ለመከላከል
በወጣው ደንብ ቁጥር 180/2017 ላይ በየደረጃው ለሚገኙ የተቋማቱ አመራሮች፣ አስተባባሪዎች፣ ባለሙያዎች እና ባለድርሻ አካላት በባለስልጣኑ የመሰብሰቢያ አዳራሽ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና አካሄደ። 

የአከባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ዲዳ ድሪባ አዲስ አበባ ከተማ የአፍሪካ ከተሞች መዲና እንደመሆንዋ ስሟን የሚመጥን ንጹህ ወንዝ ጤናማ ህይወት የተላበሰች ከተማ ለማድረግ ትልቅ ተልዕኮን አንግቦ በመስራት ላይ ይገኛል ያሉት ኃላፊዉ ልማት ከአካባቢ ጥበቃ ጋር ይዋሀድ ዘንድ የወንዞች ዳርቻ ልማትን እና ብክለት ለመከላከል ለመጠበቅ ደንቡ መውጣቱን ገልጸዋል።

የከተማዋን የወንዞች ዳርቻ ማልማት፣ መንከባከብ እና ከብክለት የጸዳ ለማድረግ ዘርፈ ብዙ ስራዎች መስራት ከሁሉም ባለድርሻ አካል የሚጠበቅ መሆኑን በማንሳት ለዚህም ይረዳ ዘንድ በቀጣይ ለከተማው ህብረተሰብ ፣ባለድርሻ አካላትና አደረጃጀቶች ስለ ደንቡ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኮች በስፋት እንደሚያዘጋጅ በመግለጽ መድረኩን በይፋ አስጀምረዋል።

በመድረኩ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ በወንዞች ዳርቻ ዙርያ ሰፊ ጥናቶችን በማጥናት ለማስተዳደር አመቺ እንዲሆን ደንቡን በማጸደቅ ተግባራዊነቱን ለማስጠበቅ በጋራ ለመስራት ሂደቱ መጀመሩን በማንሳት የከተማዋን የወንዝ ተፋሰስ ፅዱ፣ ውብ እና ምቹ ሆነው አገልግሎት ላይ እንዲውሉ በየደረጃው ላሉ አካላት ግንዛቤ መፍጠር ተቀዳሚ ተግባር እንደሚሆን ገልጸዋል።
 
በመቀጠልም የአዲስ አበባ ወንዞች ብክለት የሚገኙበትን ደረጃ እንዲሁም ደንቡ የወጣበት ምክንያት እና  ደንብ ቁጥር 180/2017 ቀርቦ ግንዛቤ ተፈጥሮበታል።
 
በመጨረሻም የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ ንጋቱ ዳኛቸው ወንዞቻችን የብክለት ምክንያት ሳይሆኑ የኢኮኖሚያችን ምንጭ እንዲሆን ለህብረተሰቡ ግንዛቤ በበቂ መንገድ በመፍጠር ለህጉ ተገዢ ባልሆኑ አካላት ላይ እርምጃዎችን በመውሰድ ደንብ የማስከበር ተልዕኮውን ተግባራዊ እንደሚደረግ አስገንዝበዋል።

የአከባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ ሙሉቀን ዮናስ እንዳሉት ከባለድርሻ ተቋማት ጋር በመቀናጀት የወንዝ ዳርቻዎችን በማልማት ከተማዋን አለም አቀፍ ደረጃዎች ያሟላች ለማድረግ እንደሚሰሩ ተናግረዋል።

የግንዛቤ ስልጠናው በነገው እለትም ለፈፃሚ አካላቱ ቀጥሎ የሚውል ሲሆን በቀጣይም እስከ ህብረተሰቡ ድረስ በየደረጃው እንደሚወርድ ተገልጿል።

ዘገባው ፦ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ነው።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments