በወንዝና ወንዝ ዳርቻዎች ላይ የሚደርሱ ብክለቶች...

image description
- In code inforcement    0

በወንዝና ወንዝ ዳርቻዎች ላይ የሚደርሱ ብክለቶችን ለመከላከል ይፋ በሆነው ደንብ ላይ ግንዛቤ ተፈጠረ።

በወንዝና ወንዝ ዳርቻዎች ላይ የሚደርሱ ብክለቶችን ለመከላከል ይፋ በሆነው ደንብ ላይ ግንዛቤ ተፈጠረ። 

 21/6/2017 ዓ.ም
       ****የአዲስ አበባ****

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ፣ከአከባቢ ጥበቃ ባለስልጣን፣ መንገዶች ባለስልጣን እና ከተማ ውበትና አረንጓዴ ልማት ቢሮ በቅንጅት ለመስራት የሚያስችል  የወንዞች ዳርቻ ልማት እና ብክለት መከላከል ደንብ ቁጥር 180/2017   አስመልክቶ ለሁለት ቀናት ሲሰጥ የነበረው የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተጠናቀቀ።

በልጠናው የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ ንጋቱ ዳኛቸው ባለስጣኑ ከጊዜ ወደ ጊዜ አቅሙን በማጎልበቱ የከተማ አስተዳሩን ልማቶች ለመጠበቅ  ተልዕኮዎች እየተሰጡት መሆኑን ጠቅሰው፤  የወንዞች ዳርቻ ልማት እና ብክለት መከላከል ዙሪያ በወጣው ደንብ  ላይ የተሰጠንን  የስራ ተልዕኮ ለመወጣት የግንዛቤ ፈጠራ አስፈላጊ በመሆኑ  በየደረጃው ግንዛቤ ፈጠራው እንደሚቀጥል አፅኖት ሰጥተዋል።

 በስልጠናው የወንዝና ወንዝ ዳርቻን ስለማልማትና ከብክለት ስለመከላከል፣ ስለ ተከለከሉ ተግባራት እንዲሁም ቅንጅታዊ አሰራር ስለቅጣት ዓይነቶች በሰፊው ገለፃ ተደርጓል።

ለማህበረሰቡ ከሚሰጠው ግንዛቤ በኃላ በቸልተኝነት ደንቡን ተላልፎ በሚገኝ አካል ላይ ዝቅተኛው የገንዘብ ቅጣት ሁለት ሺህ ብር ሲሆን ከፍተኛው እስከ አንድ ሚሊዮን ብር ድረስ የሚያስቀጣ እንደሆነ በደንቡ ተገልጿል።

የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናውን የደንብ ማስከበር ባለስልጣን የመስክ ክትትል ቁጥጥር ኦፊሰሮች ፣ የባለስልጣኑ ባለሙያዎች ፣ የከተማ ውበትና አረንጓዴ ልማት ቢሮ አመራሮችና ባለሙያዎች ተሳታፊ ሆነዋል።

በመጨረሻም ከሰልጣኞች አስተያየትና ጥያቄዎች ተነስተው የደንብ ማስከበር ባለስልጣን እና የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ምክትል ሀላፊዎች ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል።

ዘገባው፦ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ነው።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments