ስልታዊ ዕቅድ እና አሰራርን መዘርጋት ብልሹ አሰ...

image description
- In code inforcement    0

ስልታዊ ዕቅድ እና አሰራርን መዘርጋት ብልሹ አሰራርን ለመከላከል ዋነኛው መንገድ እንደሆነ ተገለፀ::

ስልታዊ ዕቅድ እና አሰራርን መዘርጋት ብልሹ አሰራርን ለመከላከል ዋነኛው መንገድ እንደሆነ ተገለፀ::

            የካቲት 24/2017 ዓ.ም
                   ****አዲስ አባባ****

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ለልደታ ክ/ከተማ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት በስነ-ምግባር፣ ፀረ-ሙስና እና መልካም አስተዳደር ዙሪያ ለወረዳ ጽ/ቤት ኃላፊ ፣ተባባሪ አካላት እና ፓራ-ሚሊተሪ ኦፊሰሮች በክ/ከተማው የመሰብሰቢያ አዳራሽ ግምገማዊ ስልጠና ሰጠ።

"ስነ-ምግባር እና መልካም አስተዳደር ለተሻለ አገልግሎት" በሚል መሪ-ቃል ግምገማዊ ስልጠና የሰጡት የባለስልጣኑ የስነ-ምግባርና የፀረ ሙስና ዳይሬክተር አቶ እዮብ ከበደ ተቋሙ የመልካም አስተዳደር እና ብልሹ አሰራርን ለመከላከል ግንዛቤ ለማስጨበጥ የተያዘው ተግባር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል እና በቀጣይ የስነ-ምግባር ችግር በሚታይባቸው ላይ የሚወሰደው እርምጃ እንደሚቀጥል ገልፀዋል።

በግምገማዊ ስልጠና ሰነዱ ላይ ብልሹ አሰራር፣ ስነ-ምግባራዊ አመራር፣ የጥቅም ግጭት እና ሙስና ለመከላከል ስለሚከናወኑ ስልታዊ አሰራሮች እና ቀጣይ እቅዶች ላይ ማብራሪያ ነጥቦች ተካቶበታል።

በስልጠናው ላይ የተገኙት ኦፊሰሮች እና ሌሎች ተሳታፊ አካላት የተለያዩ ጥያቄዎችና ሀሳብ አስተያየቶችን በማንሳት ከመድረክ ሰፊ ማብራሪያዎች እና ምላሽ በመስጠት በማጠቃለያውም የልደታ ክ/ከተማ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት የስልጠና ቡድን መሪ አቶ ደምሳሽ መሳፍንት ኦፊሰሩ ሙስናን በመከላከል በኩል ከፍተኛ ድርሻ እንዳለው በመግለጽ እየተሰጠ በሚገኘው የአቅም ግንባታ ስልጠና እራሱን በማብቃት ሙስናና ብልሹ አሰራሮችን ለመከላከል ስልታዊ አሰራሮችን ማጠናከር እንደሚገባ ገልፀዋል።

ዘገባው፦ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ነው።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments