
የወንዞች ዳርቻ ልማት እና ብክለት ለመከላከል በወጣዉ ደንብ ቁጥር 180/2017 ላይ የአሰልጣኞች ስልጠና ተሰጠ
የወንዞች ዳርቻ ልማት እና ብክለት ለመከላከል በወጣዉ ደንብ ቁጥር 180/2017 ላይ የአሰልጣኞች ስልጠና ተሰጠ።
26/06 /2017 ዓ.ም
****አዲስ አበባ****
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን የስልጠናና የቅድመ መከላከል ዘርፍ ከአከባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ጋር በመተባበር
የወንዞች ዳርቻ ልማትን እና ብክለት ለመከላከል
በወጣው ደንብ ቁጥር 180/2017 ላይ የሁለቱ ተቋማት ኃላፊዎች በተገኙበት የአሰልጣኞች ስልጠና በባለስልጣኑ መሰብሰቢያ አዳራሽ አካሄደ።
በመድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ በከተማችን የሚገኙ ትላልቅና ትናንሽ ወንዞች ለልማት ውለው ለህብረተሰቡ መገልገያና ለቱሪስት መስብ እንዲሆኑ በርካታ ተግባራት በከተማ አስተዳደሩ እየተከናወነ እንደሚገኝ ገልጸዋል።
ወንዞችን እና የወንዝ ዳርቻዎችን ከብክለት ጽዱ ለማድረግ ሁለቱም ተቋማት በጋራ በመቀናጀት ለመከላከልና የተሰጠውን ተልዕኮ ለመወጣት ዕውቀትና ልምድና ባለቸው አሰልጣኞች ስልጠናውን በመስጠትና ወደ ታች በማውረድ በየደረጃው ላሉ አካላትና ለከተማው ነዋሪዎች በቂ ግንዛቤ በመፍጠር ወንዝ ዳርቻዎችን እንዳይበከሉ ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል ።
በመድረኩ የተገኙት የአከባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ም/ስራ አስኪያጅ አቶ ሙሉቀን ዮናስ የከተማችንን የአካባቢ ብክለትን ለመከላከል ከተማዋን ፅዱ ፣ አረንጓዴ እና ለነዋሪዎቿ ምቹ ለማድረግ በከተማዋ ዉስጥ የሚገኙ ወንዝ ዳርቻዎች የማልማት ስራ እየተከናወነ ሲሆን ንፁህና ጤናማ አካባቢ እንዲሆኑ እና እንዳይበከሉ ለማድረግና ጥበቃ በማድረግ ለመከላከልና ለመቆጣጠር ይህ ደንብ አስፈላጊ መሆኑን ተናግረዋል።
በመድረኩ የአዲስ አበባ ከተማ ወንዞች ብክለት በአካባቢ እና በጤና ላይ የሚያደርሰው ጉዳት እና መፍትሔዎች እንዲሁም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የወንዞች ዳርቻ ልማት እና ብክለት መከላከል ደንብ ቁጥር 180/2017 ቀርቦ ግንዛቤ ተፈጥሮበታል።
ለማህበረሰቡ ግንዛቤ ከተፈጠረ በኃላ በቸልተኝነት ደንቡን ተላልፎ በሚገኝ አካል ላይ ዝቅተኛው የገንዘብ ቅጣት ሁለት ሺህ ብር ሲሆን ከፍተኛው እስከ አንድ ሚሊዮን ብር ድረስ የሚያስቀጣ እንደሆነ በደንቡ ተገልጿል።
በስልጠናው ማጠቃለያም የደንብ ማስከበር ባለስልጣን የስልጠናና ቅድመ መከላከል ዘርፍ ኃላፊና ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ ንጋቱ ዳኛቸው የወንዝ ዳርቻ ልማት እና ብክለትን መከላከል ዙሪያ በወጣው ደንብ ላይ የተሰጠንን የስራ ተልዕኮና ኃላፊነት ለመወጣት ግንዛቤ መፍጠር አስፈላጊ በመሆኑ ሰልጥኖ አሰልጣኞች በየደረጃው በመውረድ የግንዛቤ ማስጨበጥ ስራውን አጠናክረው ማስቀጠል እንደሚገባ አሳስበዋል።
በመጨረሻም ከተሳታፊዎች ጋር ሰፊ ውይይት በማድረግ ለተነሱ ሀሳብና ጥያቄዎች ከመድረኩ ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቶበት ቀጣይ የስራ አቅጣጫ በባለስልጣኑ ም/ስራ አስኪያጅ አቶ ንጋቱ ዳኛቸው ተሰጥቷል።
ዘገበው ፡-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳሬክቶሬት ነው፡፡
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments