ፍሳሽ ቆሻሻን በመልቀቅ ወንዝ የበከለ ድርጅት 3...

image description
- In code inforcement    0

ፍሳሽ ቆሻሻን በመልቀቅ ወንዝ የበከለ ድርጅት 300 ሺህ ብር ተቀጣ

ፍሳሽ ቆሻሻን በመልቀቅ ወንዝ የበከለ ድርጅት 300 ሺህ ብር ተቀጣ

             28/06/2017 ዓ.ም
               ****አዲስ አበባ***

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣ ከአከባቢ  ጥበቃ ባለስልጣን ጋር በመቀናጀት በዛሬው ዕለት በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 05 ይህን ደንብ ተላልፎ በተገኘ ቫይብስ ሆቴልና ስፓ/Vibes Hotel & Spa/ ድርጅት ላይ በደንብ ቁጥር 180/17 የቅጣት ሰንጠረዥ 1 ተራ ቁጥር 3 ያልተጣራ ፍሳሽ ቆሻሻ ወደ ወንዝ የለቀቀ ድርጅት 300,000 (ሶስት መቶ ሺህ) ብር በመቅጣት አስተዳደራዊ እርምጃ ወስዷል።

ባለስልጣኑ በደንብ ቁጥር 180/2017 ላይ ከአከባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ጋር በመተባበር በተደጋጋሚ በመገናኛ ብዙኃንና በመድረኮች ለህብረተሰቡ ግንዛቤ ፈጥሯል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ በጀት በመመደብ ከተማዋን ውብ ጽዱና ለነዋሪዎቿ  ምቹ ለማድረግ የወንዝ ዳርቻና የኮሪደር ልማት 7/24 በመስራት የወንዞች ዳርቻ የማስዋብ ስራዎችን  እየሰራ መሆኑ ይታወቃል።

ህብረተሰቡም መንግስት ከፍተኛ ወጪ አውጥቶ ያለማቸውን ሀብቶች እንዲንከባከብና ደንብ ተላልፎ የሚገኝ አካል ሲገኝ በ9995 ጥቆማ እንዲሰጥ ጥሪውን አቅርቧል።

ባለስልጣኑ በቀጣይ በየትኛውም የኮሪደርና የወንዝ ዳርቻ ልማቶች ዙሪያ የሚደረጉ የደንብ መተላለፎችን እንደማይታገስና እርምጃውንም አጠናክሮ እንደሚቀጥል አሳውቋል።

ዘገባው:- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኔኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ነው።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments