
ግንፍሌ ወንዝ ውስጥ ቆሻሻ የጣለው ድርጅት 100 ሺህ ብር ተቀጣ
ግንፍሌ ወንዝ ውስጥ ቆሻሻ የጣለው ድርጅት 100 ሺህ ብር ተቀጣ
28/06/2017 ዓ.ም
****አዲስ አበባ***
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣ ከአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ጋር በመተባበር በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 07 ግንፍሌ ወንዝ ውስጥ ቆሻሻ የጣለው የኢትጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ጠቅላይ ቤተክነት የሠንበት ት/ቤት ማደራጃና መምሪያ የማህበረ ቅዱሳን ተቋም በከተማ አስተዳደሩ የወጣው ደንብ ቁጥር 180/2017 በመተላለፍ ደረቅ ቆሻሻን ወደ ወንዝ በመጣሉ 100,000/አንድ መቶ ሺህ/ ብር ተቀጥቷል።
ባለስልጣኑ በደንብ ቁጥር 180/2017 ላይ ከአከባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ጋር በመተባበር በተደደጋጋሚ በመገናኛ ብዙኃንና በመድረኮች ለህብረተሰቡ ግንዛቤ መፍጠሩ ይታወሳል።
ባለስልጣኑ በቀጣይ የወንዝ ዳርቻ ልማቶች ዙሪያ ደንብ የሚተላለፉ ግለሰቦችና ተቋማት ላይ የሚወስደውን እርምጃ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አሳውቋል።
ዘገባው:- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኔኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ነው።
ለተጨማሪ መረጃ፦
የሶሻል ሚዲያ ገፆቻችን ፎሎው፣ላይክ እና ሰብስክራይብ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ።
ዌብሳይት ገፃችን፦
https://www.aacea.gov.et/
የፌስ ቡክ ገፃችን፦
https://www.facebook.com/profile.php?id=100082525711518&mibextid
የቴሌግራም ቻናላችን
https://t.me/codeenforcement
የዩቱብ ቻናላችን
https://youtube.com/@A.A.C.ACODEENFORCEMENT
የቲክቶክ አካውንታችን
https://www.tiktok.com/@addisababacodeenforcemen
ለማንኛውም የደንብ መተላለፍ ጥቆማ ነፃ የስልክ መስመር 9995 ይጠቀሙ
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments