ኦፊሰሩን በስነ-ምግባር ለማነጽ የግንዛቤ ስልጠ...

image description
- In code inforcement    0

ኦፊሰሩን በስነ-ምግባር ለማነጽ የግንዛቤ ስልጠናዎች ሚናቸው የላቀ መሆኑ ተገለፀ

ኦፊሰሩን  በስነ-ምግባር ለማነጽ የግንዛቤ ስልጠናዎች ሚናቸው የላቀ መሆኑ ተገለፀ

              28/06/2017 ዓ.ም
             ****አዲስ አበባ****

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን  ለልደታ  ክፍለ ከተማ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት ኦፊሰሮችና ሽፍት መሪዎች "መልካም አስተዳደር  ለተሻለ አገልግሎት" በሚል መሪ ቃል በክፍለ ከተማው አዳራሽ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ።

በባለስልጣኑ የስነ-ምግባርና ጸረ-ሙስና ዳይሬክተር አቶ እዮብ ከበደ የቀረበው ሰነድ ብልሹ አሰራርና የስነምግባር ጉድለት በመልካም አስተዳደር ላይ የሚሳድረውን ተፅኖ እና ችግሩን መፍታት በሚገባው አቅጣጫ ላይ ስልጠና ተሰጨጥቷል።

በሰነዱ መነሻነት ከተሳታፊዎች ጋር ውይይት የተደረገ ሲሆን ለቀረቡ ሀሳብና አስተያየቶች ከመድረኩ ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቶበታል።

በተጨማሪም የወንዝ ዳር ብክለትን ለመከላከል በወጣው ደንብ ቁጥር 180/2017 ላይም በክፍለ ከተማው የአከባቢ ጥበቃ ጽ/ቤት ቡድን መሪ አቶ ለሜሳ ደበላ ደንቡና የቅጣት ሰንጠረዡ ቀርቦ ግንዛቤ ተፈጥሮበታል።

በመጨረሻም የክፍለ ከተማው ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት ወረዳዎች በመጀመሪያ ግማሽ ዓመት የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ ወረዳዎች የጽ/ቤት ኃላፊው አቶ ደሳለኝ እውቅና ሰጥተዋል።

ዘገባው:-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኔኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ነው።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments