
ባለስልጣኑ የየካቲት ወር እቅድ አፈጻጸሙን እየገመገመ ነው
ባለስልጣኑ የየካቲት ወር እቅድ አፈጻጸሙን እየገመገመ ነው
29 - 06 - 2017 ዓ.ም
**** አዲስ አበባ****
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የ2017 በጀት ዓመት የካቲት ወር እቅድ አፈጻጸሙን የተቋሙን የባለስልጣኑ ከፍተኛ አመራሮች ፣ዳይሬክተሮች የ11ዱም ክፍለ ከተማ እና የወረዳ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት ሀላፊዎች በተገኙበት እየገመገመ ይገኛል ።
በመድረኩ ንግግር ያደረጉት የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ በወሩ የደንብ ጥሰቶችን በመከላከልና በመቆጣጠር፣እርምጃ አወሳሰድና የ6ኛ ዙር የፓራ -ሚሊተሪ ኦፊሰሮች ምልመላ በተመለከተ የተሰሩ ስራዎች በትኩረት እንደሚገመገሙ አመላክተዋል።
በመድረኩ የባለስልጣኑ የቀጣይ ስራ የትኩረት አቅጣጫዎች እንደሚቀመጥ ይጠበቃል።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments