
"የከተማ አስተዳደሩ የሰጠንን ተልዕኮ በአግባቡ መፈፀም ይጠበቅብናል" ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ
"የከተማ አስተዳደሩ የሰጠንን ተልዕኮ በአግባቡ መፈፀም ይጠበቅብናል" ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ
የካቲት 29 /2017 ዓ.ም
**** አዲስ አበባ****
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳዳ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ከፍተኛ አመራሮች፣ የ11ዱም ክፍለ ከተማ እና የ119ኙ የወረዳ ሀላፊዎች እና የማዕከሉ ዳይሬክተሮች በድን መሪዎች በተገኙበት የካቲት ወር የስራ ክንውን ግምገማ አካሄደ።
በመድረኩ የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ የከተማ አስተዳደሩ በሰጠን ተልዕኮ እና በጣለብን እምነት መሠረት የደንብ መተላለፎችን በመከላከል፣ በመቆጣጠርና እርምጃ በመውሰድ ደንብ ቁጥር 167/2016 እና 180/2017 በመፈጸም ተልዕኮውን በአግባቡ መወጣት እንደሚገባ አሳስበዋል።
የባለስልጣኑ ምክትል ስራ-አስኪያጅ አቶ ከፍያለው ታደሰ በበኩላቸው የደንብ መተላለፎችን በተመለከተ እርምጃ መውሰድ ብቻ ሳይሆን የፈፀመው አካል ተገቢውን ቅጣት ማግኘተ እንዳለበትና የተጠናከረ የመረጃ አያያዝ ስርዓት ማሳደግ እንደሚገባ ገልፀዋል
የባለስልጣኑ ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ ንጋቱ ዳኛቸው በበኩላቸው የተቋሙ ገጽታ ለመቀነስ የተጠናከረ የሶሻል ሚዲያ ስራ እና ህብረተሰቡ ያሳተፈ ስራ በመግባባት መስራት እንደሚያስፈልነግ ።
በግምገማው በአገልግሎት አሰጣጥ፣ በመልካም አስተዳደር ዙርያ የተሰሩ ስራዎች በደንብ መተላለፍ የቅድመ መከላከልና የእርምጃ አወሳሰድተግባራትና የ6ኛ ዙር የፓራ ሚሊተሪ ኦፊሰሮች ምልመላን አስመልክቶ የተሰሩ ሰራዎችን በተመለከተ የተሰሩ ሰራዎች ላይ ግምገማው ተካሂዷል።
በመድረኩ ከክፍለ ከተማ የልደታ፣የነፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተሞች እና ከወረዳ የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 14 እና የጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 የተሰሩ ሰራዎችን ሪፖርት በዝርዝር እንደማሳያ አቅርበዋል።
በእለቱ በ11 ክፍለ ከተሞች ሙስናና ብልሹ አሰራርን አስመልክቶ እየተሰጠ ያለውን የስልጠና ሪፓርት አስመልክቶ የባለስልጣኑ የስነ-ምግባርና የፀረ-ሙስና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ እዮብ ከበደ በሶሻል ሚዲያ የሚለቀቁ የስነ ምግባር ግድፈቶች እንደ ማሳያ በማቅረብ በቀጣይ መስተካከል እንዳለበት አሳስበዋል።
በባለስልጣኑ በየካቲት ወር የተሰሩ ሰራዎችን አስመልክቶ ሪፖርት ያቀረቡት የባለስልጣኑ የእቅድና በጅት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ኮለኔል አድማሱ ተክሌ በሪፖርቱ በቴክኖሎጂ አጠቃቀምና ፣በወንዞች ዳርቻ ልማትን አስመልክቶ እየተሰሩ ያሉ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናዎች በትኩረት መሰራቱን ጠቅሰዋል።
በመድረኩ የ6ኛ ዙር የአዲስ ምልምል ኦፊሰሮች ምልመላ ሂደት በእቅዱ መሠረት በጥሩ ሁኔታ እየተሰራ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን የቀጣይ ስራዎች በጥንቃቄ መሰራት እንዳለበት ተመላክቷል።
በመጨረሻም የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ የቀጣይ ስራ የትኩረት አቅጣጫዎች በማስቀመጥ መድረኩ ተጠናቋል።
ዘገባው:- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኔኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ነው።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments