ባለስልጣኑ የመሬት ባንክ የገባ መሬት በመውረር...

image description
- In code inforcement    0

ባለስልጣኑ የመሬት ባንክ የገባ መሬት በመውረር በተገነባ ግንባታ ላይ እርምጃ መውሰዱን አስታወቀ

ባለስልጣኑ የመሬት ባንክ  የገባ መሬት በመውረር በተገነባ ግንባታ ላይ እርምጃ መውሰዱን አስታወቀ 

       የካቲት 30/2017 ዓ.ም  
         ****አዲስ አበባ****

የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ወረዳ 2 መሬት ባንክ ገብቶ ሲጠበቅ የነበረ 1000 ካ.ሜ. የህዝብና የመንግስትን መሬት በህገወጥ መንገድ ሁለት ግለሰቦች የ2012 ዓ.ም ካርታ  አለን በማለትና ከወረዳው የግንባታ ፍቃድ በማውጣት ቦታውን አጥረው ህገ-ወጥ  ግንባታ ለመገንባት ሙከራ ሲያደርጉ መያዛቸው ተገለፀ  ።

ባለስልጣኑ መሬት ባንክ ገብቶ ሲጠብቀው በነበረን መሬት ላይ የተገነባውን ግንባታ የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 ደንብ ማስከበረ ጽ/ቤት ከክፍለ ከተማና ከወረዳ አመራሮች ጋር በመቀናጀት የጸጥታ አካላትን በማሳተፍ ግንባታውን በማፍረስ  የመንግስትና የህዝብ መሬት ወደ ነበረበት እንዲመለስ ማድረጉ አስታውቋል።

ጥፋተኞችን ለህግ  ለማቅረብ መረጃውን በማደራጀት በቁጥጥር ስር በማዋል በሊዝ አዋጁ ተጠያቂ ለማድረግ በሂደት ላይ መሆናቸው ተጠቁሟል።

ባለስልጣኑ በህገ-ወጦች ላይ የሚወስደውን እርምጃ አጠናክሮ  እንደሚቀጥል የገለፀ ሲሆን ደንብ የሚተላለፉ አንዳንድ ግድ የሌሽ ግለሠቦችን ልማት ወዳዱ  የከተማችን ነዋሪዎች በ9995 ነፃ የስልክ መስመር ጥቆማ እንዲሰጡ ጥሪውን ያቀርባል ።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments