የመፀዳጃ ቤት ፍሳሽ ከዋና ፍሳሽ መስመር በማገና...

image description
- In code inforcement    0

የመፀዳጃ ቤት ፍሳሽ ከዋና ፍሳሽ መስመር በማገናኘት ወደ ወንዝ እንዲገባ ያደረጉ የንግድ ቤቶችን 600 ሺህ ብር ተቀጡ

የመፀዳጃ ቤት ፍሳሽ ከዋና ፍሳሽ መስመር በማገናኘት ወደ ወንዝ እንዲገባ ያደረጉ የንግድ ቤቶችን 600 ሺህ ብር ተቀጡ

           30/06/2017 ዓ.ም
           ****አዲስ አበባ***

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣ ከአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ጋር በመተባበር በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 የመፀዳጃ ቤት ፍሳሽ ከዋና መስመር ትቦ ጋር ባገናኙ ሁለት የንግድ ቤቶች በደንብ ቁጥር 180/2017 መሰረት እያንዳንዳቸው 300,000/ሶስት መቶ ሺህ/ ብር  በድምሩ 600,000/ስድስት መቶ ሺህ ብር በመቅጣት እርምጃ መውሰዱን አስታወቀ።

ባለስልጣኑ ህብረተሰቡ ማንኛውም አይነት ፍሳሽ ቆሻሻ ወደ ወንዝ ከመልቀቅና ደረቅ ቆሻሻ ወንዝ ውስጥ ከመጣል እንዲቆጠቡ አሳስቧል። 

ተቋሙ ድርጊቱን በሚፈፅሙ ግለሰቦችና ተቋማት በደንብ ቁጥር 180/2017 መሠረት እርምጃውንም አጠናክሮ እንደሚቀጥል አሳውቋል።

የከተማ አስተዳደሩ  የአዲስ አበባ ወንዞች ከመጥፎ ሽታ ተላቀው የመዝናኛ ቦታዎች እዲሆኑ የጀመረው ስራ ዳር ለማድረስ ደንብ በማስከበር የበኩሉን ድርሻ እንደሚወጣ ገልጿል።

ህብረተሰቡም ደንቡን ተላልፎ የሚገኝ አካል ሲመለከት በነፃ የስልክ መስመር 9995 ጥቆማ እንዲሰጥ መልዕክቱን ያስተላልፋል።

መረጃው:- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኔኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments