ባለስልጣኑ በዛሬው እለት ፍሳሽ ቆሻሻ ወደ ወንዝ...

image description
- In code inforcement    0

ባለስልጣኑ በዛሬው እለት ፍሳሽ ቆሻሻ ወደ ወንዝ የለቀቁ ግለሰቦችና ተቋማትን 2,300,000/ሁለት ሚሊየን ሶስት መቶ ሺህ/ ብር መቅጣቱ አስታወቀ

ባለስልጣኑ በዛሬው እለት ፍሳሽ ቆሻሻ ወደ ወንዝ የለቀቁ ግለሰቦችና ተቋማትን 2,300,000/ሁለት ሚሊየን ሶስት  መቶ ሺህ/ ብር መቅጣቱ አስታወቀ

                    01/07/2017 ዓ.ም
                   ****አዲስ አበባ****

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣ ከአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ጋር በመተባበር ፍሳሽ ቆሻሻ ወደ ወንዝ የለቀቁ ድርጅቶችና ግለሰቦች  በደንብ ቁጥር 180/2017 መሰረት የገንዘብ ቅጣቶች  በመቅጣት አስተዳደራዊ እርምጃ መውሰዱን አስታወቀ፡፡

በዛሬው እለትም በቂርቆስ ክፍለ ከተማ 3 ድርጅቶች እያንዳንዳቸው 300,000/ሶስት መቶ ሺህ/ ብር  በድምሩ 900,000/ዘጠኝ መቶ ሺህ ብር እና አንድ ግለሰብ 100,000/አንድ መቶ ሺህ/ ብር  በድምሩ 1 ሚሊዮን ብር ቀጥቷል፡፡

በተያዘ ዜና በአዲስ ከተማ  ክፍለ ከተማ 700 ሺህ ብር ፤በነፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ 300 ሺህ ብር ፤ በጉለሌ ክፍለ ከተማ 300 ሺህ ብር  በድምሩ በዛሬው እለት 2300,000/ሁለት ሚሊየን ሶስት  መቶ ሺህ ብር/  በመቅጣት አስተዳደራዊ እርምጃ መውሰዱን  አስታውቋል።

ባለስልጣኑ ተቋማት እና ግለሰቦች  ማንኛውም አይነት ፍሳሽ ቆሻሻ ወደ ወንዝ በመልቀቅም ሆነ ደረቅ ቆሻሻ ወንዝ ውስጥ በመጣል ደንብ በመተላለፍ ከሚወሰደው የቅጣት እርምጃ እራሳቸውን እንዲጠብቁ አሳስቧል። 

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን  ድርጊቱን በሚፈፅሙ ግለሰቦችና ተቋማት ላይ በደንብ ቁጥር 180/2017 መሠረት የሚወሰደው እርምጃ አጠናክሮ እንደሚቀጥል  አሳውቋል።

ህብረተሰቡም ደንቡን ተላልፎ የሚገኝ አካል ሲመለከት በነፃ የስልክ መስመር 9995 ጥቆማ እንዲሰጥ ጥሪውን  አስተላልፏል።

መረጃው:- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኔኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ነው።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments