
በደንብመከላከልለ180/2017 ላይ ለአምራችና አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶች ግንዛቤ ተፈጠረ።
በደንብመከላከልለ180/2017 ላይ ለአምራችና አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶች ግንዛቤ ተፈጠረ።
02/07 /2017 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ከአከባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ጋር በመተባበር "ንፁህ ወንዝ ለጤናማ ህይወት" በሚል መሪ ቃል
የወንዝ ዳርቻዎች ልማትን እና ብክለት ለመከላከል በወጣው ደንብ ቁጥር 180/2017 ለአምራችና አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶች የሁለቱ ተቋማት አመራሮች በተገኙበት የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና በአዲስ አበባ ከንቲባ ጽ/ቤት አዳራሽ አካሄደ።
በመድረኩ ንግግር ያደረጉት የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ እንደገለፁት በከተማው አስተዳደር ስር የሚገኙ ተቋማት በሙሉ 7/24 ስራዎችን በማከናወን የከተማውን እድገት ለማፋጠን እየተጉ ይገኛሉ።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን እንዲያስፈጽም የተሰጡትን ደንቦች ሁሉ በማስከበር ተልዕኮውን በአግባቡ እየተወጣ እንደሚገኝ ዋና ስራ አስኪያጁ ገልጸዋል።
አክለውም በዛሬው ዕለት "ንጹህ ወንዝ ለጤናማ ህይወት!" በሚል መሪ ቃል ለከተማዋ ልማትና እድገት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ከምታበረክቱ አምራችና አገልግሎት ሰጪ ድርጅት ጋር በደንብ ቁጥር 180/2017 መግባባት ላይ በመድረስ ከፍተኛ በጀት የወጣበትን የህዝብና የሀገር ሀብቶችን በጋራ መጠበቅ ይገባል ሲሉ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።
ሌላው በመድረኩ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአከባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ዲዳ ድሪባ በከተማችን የሚገኙ ወንዞችን የኢኮኖሚያችን ግብዓትና የህዝባችን መዝናኛ ስፍራ ለማድረግ የጀመረውን ልማት ለማስጠበቅ ደንብ ቁጥር 180/2017 ወደ ስራ በማስገባትና በማስፈጸም ላይ እንደሚገኝ ገልጸዋል።
ከተማችን ከግብር ከፋዮች በምታገኘው ገቢ የኮሪደር ልማትን ጨምሮ በርካታ ፕሮጀክቶችን በማከናወን ላይ ትገኛለች። እነዚህን የለሙና የተገነቡ ስፍራዎች ለመጠበቅ የተለያዩ ደንቦች ጸድቀዉ ወደ ስራ ተገብቷል።
በቀጣይም ለህብረተሰቡ የግንዛቤ ማስጨበጥ ስራው ተጠናክሮ የሚሰራ ሲሆን ደንቡን ተላልፈው በሚገኙ አካላት ላይ አስተዳደራዊ እርምጃ መውሰድ መጀመሩን የአከባቢ ጥበቃ ዋና ስራ አስኪያጅ ገልጸዋል።
በመድረኩ የአዲስ አበባ ከተማ ወንዞች ብክለት በአካባቢ እና በጤና ላይ የሚያደርሰው ጉዳት እና መፍትሔዎች እንዲሁም የወንዞች ዳርቻ ልማት እና ብክለት ለመከላከል የወጣው ደንብ ቁጥር 180/2017 እና የቅጣት ሰንጠረዥ በዝርዝር ቀርቦ ግንዛቤ ተፈጥሮበታል።
በደንቡ ዙሪያ በተለያዩ አግባቦች ለህብረተሰቡ ግንዛቤ የማስጨበጥ ስራዎችን በተደጋጋሚ ተጠናክሮ የሚቀጥል ሆኖ ደንቡን ተላልፎ በሚገኝ አካላትና ተቋማት ላይ ዝቅተኛው የገንዘብ ቅጣት ሁለት ሺህ ብር ሲሆን ከፍተኛው እስከ አንድ ሚሊዮን ብር ድረስ የሚያስቀጣ እንደሆነ በሰነዱ ተመላክቷል።
በመድረኩ ተሳታፊ የሆኑ አምራችና አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶች ከተማዋን ለማልማት በሚደረግ ሂደት ውስጥ ኃላፊነታችንን መወጣታችን እንደለ ሆኖ ሁለቱም ተቋማት ከቅጣቱ በፊት ግንዛቤ ላይ ትኩረት ተሰጥቶት ቢሰራበት የሚል አስተያየታቸውን ተሰጥተዋል።
በመጨረሻም ከተሳታፊዎች ጋረ ሰፊ ውይይት በማድረግ ለተነሱ ሀሳቦችና ጥያቄዎች ከመድረኩ ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቶበታል ።
ዘገበው ፡-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳሬክቶሬት ነው፡፡
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments