ባለስልጣኑ በዛሬው እለት ደንብ ቁጥር 180/20...

image description
- In code inforcement    0

ባለስልጣኑ በዛሬው እለት ደንብ ቁጥር 180/2017 የተላለፉ ድርጅቶች እና ግለሰቦች 6,700,000/ስድስት ሚሊየን ሰባት መቶ ሺህ/ ብር መቅጣቱ ገለጸ

ባለስልጣኑ በዛሬው እለት ደንብ ቁጥር 180/2017 የተላለፉ ድርጅቶች እና ግለሰቦች 6,700,000/ስድስት ሚሊየን ሰባት መቶ ሺህ/ ብር መቅጣቱ ገለጸ

               03/07/2017 ዓ.ም
             ****አዲስ አበባ****

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣ ከአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ጋር በመተባበር ፍሳሽ ቆሻሻ ወደ ወንዝ የለቀቁ ድርጅቶችና ግለሰቦችን  በደንብ ቁጥር 180/2017 መሰረት የገንዘብ ቅጣቶች  በመቅጣት አስተዳደራዊ እርምጃ መውሰዱ ገለጸ፡፡

ባለስልጣኑ በዛሬው እለት በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ 1,800,000 ብር ፤በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ 1,750,000 ብር፣ በአራዳ ክፍለ ከተማ 1,200,000 ብር፣በጉለሌ ክፍለ ከተማ 600,000 ብር ፣ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ 400,000 ብር በመቅጣት አስተዳደራዊ እርምጃ ወስዷል።

በተያያዘ ዜና በቦሌ ክ/ከተማ 450,000 ብር በኮልፌ ክ/ከተማ 400,000 ብር ፤በልደታ ክፍለ ከተማ 100,000 ብር በመቅጣት  አስተዳደራዊ እርምጃ በመውሰድ ለመንግስት ገቢ አድርጓል።

ባለስልጣኑ በአጠቃላይ በዛሬው እለት 24 ድርጅቶች እና  3 ግለሰቦች በድምሩ 6,700,000/ስድስት ሚሊየን ሰባት መቶ ሺህ/ ብር መቅጣቱ ገልጿል።

መረጃው:- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኔኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments