የወንዝ ብክለት ላይ ጠንከር ያለ የክትትልና የቁ...

image description
- In code inforcement    0

የወንዝ ብክለት ላይ ጠንከር ያለ የክትትልና የቁጥጥር ስራዎች እንደሚሰሩ ተገለፀ

የወንዝ ብክለት ላይ ጠንከር ያለ የክትትልና የቁጥጥር ስራዎች እንደሚሰሩ ተገለፀ

               04/07/2017 ዓ.ም
             ****አዲስ አበባ****

የጉለሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር "ንፁህ ወንዞች ፤ ለጤናማ ህይወት" በሚል መሪ ቃል የወንዞች ዳርቻ ልማት እና ብክለት መከላከል ዙሪያ ከክፍለ ከተማው የደንብ ማስከበርና ከአካባቢ ጥበቃ ጽ/ቤት ጋር በመሆን ከ10ሩም ወረዳ ከተወጣጡ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር ውይይት አካሄዷል።

የውይይቱ ዓላማ በየአካባቢው የሚገኙ ወንዞችን ከተለያዩ በካይ ቆሻሻዎችና ፈሳሾች ጥበቃ በማድረግ ተፈጥሮዓዊ ይዞታቸውን ይዘው እንዲፈሱ ለማስቻል እና የወንዝ ዳርቻ ልማት እና ብክለት መከላከል ደንብ ቁጥር 180/2017  ላይ የህብረተሰቡን ግንዛቤ መጨመር እንደሆነ ተገልጿል።

በመድረኩ ላይ የጉለሌ ክፍለ ከተማ ዋና  ስራ አስፈፃሚ አቶ ወልዴ ወገሴ እንደተናገሩት በክፍለ ከተማችን ብሎም በከተማችን የከተማ አስተዳደሩ የወንዝ ዳርቻ ልማት ፕሮጀክቶች በማከናወን ላይ ይገኛል ይህም ወንዞች የቆሻሻ ማስወገጃ እንደሆኑ የነበሩ ዘልማዳዊ አስተሳሰቦች በመቀየር  የህዝቦችን ተጠቃሚነት እና ኑሮን ያሻሻሉ  ዘርፈ ብዙ ስራዎች እየተሰራ እንደሚገኝ ገልፀዋል።

ዋና ስራ አስፈጻሚው አክለውም  ከተማ አስተዳደሩ  የወንዝ ዳርቻ ልማት እና ብክለት መከላከል ደንብ ቁጥር 180/2017 አውጥቶ ተግባራዊ እየተደረገ እንደሚገኝና በደንቡ ዙሪያ በማስተማር ህጉን ተላልፈው በተገኙት ላይ አስተዳደሩ ህጋዊ እርምጃ ይወስዳል ብለዋል።

የጉለሌ ክፍለ ከተማ አካባቢ ጥበቃ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዳንኤል እዮብ በበኩላቸው የወንዝ ዳርቻ ልማት እና ብክለት መከላከል ደንብ ቁጥር 180/2017 አስመልክቶ የመወያያ ሰነድ ያቀረቡ ሲሆን የህብረተሰቡን ግንዛቤ በማሳደግ ወንዞችንና የወንዝ ዳርቻዎችን በማልማት፤ ጠንካራ የብክለት ክትትልና ቁጥጥር ስራዎችን በመስራት አረንጓዴ ንፁህ ውብና  ስፍራ እንዲፈጠርና  የህግ ተከባሪነትን ለማረጋገጥ በሚሰሩ ስራዎች የክፍለ ከተማው ነዋሪዎች ተባባሪም መሆን እንዳለባቸው ገልጸዋል፡፡

የውይይቱ ተሳታፊዎች በበኩላቸው የከተማ አስተዳደሩ የወንዝ ዳርቻ ልማት ፕሮጀክት በመልማቱ የተሰማቸውን ደስታ ገልጸው የወንዞችን ብክለትን ለመከላከል  አካባቢያቸውን ንፁህ እና ማራኪ በማድረግ  በሚሰሩ ተግባራት ላይ ተሳታፎዋቸውን እንደሚያጠናክሩ ተናግረዋል፡፡


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments