
የወንዝ ዳርቻ ልማትን ከማፋጠንና ብክለትን ከመከላከል ጋር ተያይዞ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ተካሄደ
የወንዝ ዳርቻ ልማትን ከማፋጠንና ብክለትን ከመከላከል ጋር ተያይዞ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ተካሄደ
መጋቢት 4/2017 ዓ.ም
****አዲስ አበባ****
በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ የወንዝ ዳርቻ ልማትን ከማፋጠንና ብክለትን ከመከላከል ጋር ተያይዞ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ተካሂዷል።
በክፍለ ከተማው አካባቢ ጥበቃ ጽ/ቤት እና በደንብ ማስከበር ጽ/ቤት አዘጋጅነት በተካሄደው መድረክ አመራሮች፣ የደንብና የአካባቢ ጥበቃ ባለሙያዎች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው ነዋሪዎች ተገኝተዋል።
በዕለቱም በደንብ ቁጥር 180/2017 አሰራርና አደረጃጀት ዙሪያ ማብራሪያ ሰነድ ቀርቦ ከተሳታፊዎች ሀሳብና አስተያየት ተሰጥቶበታል።
የክፍለ ከተማው ምክትል ስራ አስፈጻሚና የስራና ክህሎት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ድላየሁ ታምሬ የዲፕሎማሲና የቱሪዝም ከተማ የሆነችውን አዲስ አበባ ወንዞቿን ማልማትና ከብክለት መጠበቅ የሁሉም ዜጋ ኃላፊነት ሊሆን እንደሚገባ ተናግረዋል።
አቶ ድላየሁ አክለውም ወንዞችን ከኮሪደር ልማቱ ጋር በማቀናጀት ለልማትና ለመዝናኛነት ማዋል አስፈላጊ መሆኑን አንስተዋል።
የክፍለ ከተማው አካባቢ ጥበቃ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አስፋው ፋራህ በበኩላቸው የአካባቢ ብክለትን በመከላከል የከተማዋ ወንዞችን በጋራ በማልማት የድርሻችንን እንወጣለን ብለዋል።
የክፍለ ከተማው ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት ኃላፊ መቶ አለቃ ቦጋለ አለሙ እንደገለፁት ህግና ስርዓትን በማስከበር፣ ግንዛቤ በመፍጠር እንዲሁም ህጋዊ እርምጃ በመውሰድ ወንዞችን ከብክለት ለመጠበቅ በቅንጅት መስራት አለብን ብለዋል።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments