
ባለስልጣኑ ወንዞችና የወንዞች ዳርቻ በሚበክሉ አካላትን ከድርጊታቸው እንዲታቀቡ አስጠነቀቀ
ባለስልጣኑ ወንዞችና የወንዞች ዳርቻ በሚበክሉ አካላትን ከድርጊታቸው እንዲታቀቡ አስጠነቀቀ
05/07/2017 ዓ.ም
****አዲስ አበባ****
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣ ከአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ጋር በመተባበር ወንዞችና የወንዞች ዳርቻ የበከሉ ድርጅቶችና ግለሰቦችን በዛሬው እለትም በደንብ ቁጥር 180/2017 መሰረት 3,176,000/ሶስት ሚሊየን አንድ መቶ ሰባ አምስት ሺህ/ ብር የገንዘብ ቅጣት በመቅጣት አስተዳደራዊ እርምጃ መውሰዱን አስታወቀ፡፡
ባለስልጣኑ በዛሬው እለት በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ 800,000 ብር፣ በልደታ ክፍለ ከተማ 750,000 ብር፣በነፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ 426,000 ብር ፤በቦሌ ክፍለ ከተማ 300,000 ብር፣አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ 300,000 ብር በመቅጣት አስተዳደራዊ እርምጃ ወስዷል።
በተያያዘ ዜና በኮልፌ ክ/ከተማ 300,000 ብር ፤በአቃቂ ክ/ከተማ 300,000 ብር በመቅጣት አስተዳደራዊ እርምጃ ወስዷል።
በአጠቃላይ በዛሬው እለት 7 ድርጅቶች እና 5 ግለሰቦችን በመቅጣት በድምሩ 3,176,000/ሶስት ሚሊየን አንድ መቶ ሰባ አምስት ሺህ/ ብር በመቅጣት ለመንግስት ገቢ መደረጉን ተገልጿል።
ባለስልጣኑ ወንወዞችና የወንዞች ዳርቻ በሚበክሉ አካላትን ከድርጊታቸው እንዲታቀቡ ያስጠነቀቀ ሲሆን ድርጊቱን በሚፈጽሙ አካላት ላይ የሚወስደውን እርምጃ አጠናክሮ አንደሚቀጥል አስታውቋል።
መረጃው:- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኔኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments