
አዲስ አበባን ከብልሹ አሰራርና ከደንብ መተላለፎች ለማጽዳት በትብብር መስራት እንደሚገባ ተገለፀ
አዲስ አበባን ከብልሹ አሰራርና ከደንብ መተላለፎች ለማጽዳት በትብብር መስራት እንደሚገባ ተገለፀ
መጋቢት 6/7/2017 ዓ,ም
****የአዲስ አበባ****
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ለኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ደንብ ማስከበር ፅ/ቤት ፓራ-ሚሊተሪ ኦፊሰሮች በስነ-ምግባር፣በመልካም አስተዳደር እና አገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ ስልጠና ሰጠ፡፡
ስልጠናው የሰጡት የባለስልጣኑ የስነ-ምግባር እና ፀረ ሙስና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ እዮብ ከበደ ተቋሙ በሰጠው ስልጠና ግንዛቤ መሰረት በቀጣይ የስነ ምግባር ችግሮች የሚታይባቸው ሰራተኞች ላይ የሚወሰደውን እርምጃ አጠናክረን እንደሚቀጥል ገልፀዋል፡፡
የኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ደንብ ማስከበር ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሙሉ ጌታ ጎንፋ በበኩላቸው አመራሮችና ባለሙያዎች ተቋማዊ ለውጥን ለማረጋገጥ ሙያዊ ስነ-ምግባር በመላበሰ እንደሚገባቸው ገልፀዋል።
አክለውውም ኦፊሰሩ በስልጠናው መሠረት የአመለካከት ለውጥ በማምጣት የተገልጋዩን እርካታ ማሳደግና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን መፍታት እንደሚገባቸው ተናግረዋል።
በስልጠናው የተገኙት የባለስልጣኑ የሰው ሃብት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶሰለሞን ይልማ ተቋማዊ ለውጥ ለማምጣት የተቋሙን እሴቶች፣ በመላበስ የተሰጠን ተልእኮዎችን መፈፀም እንደሚገባ አሳስበዋል።
በዕለቱ የደንብ ማስከበር አመራርና ባለሙያዎች አዲስ አበባን ከብልሹ አሰራርና ከደንብ መተላለፎችና ለማጽዳት የተለወጠ አስተሳሰብ ለተቋማዊ ለውጥ አስፈላጊ እንደሆነ በመረዳት በትብብር ሊሰሩ እንደሚገባ ተገልጿል።
በመጨረሻም ከስልጠናው ተሳታፊዎች ጋር ውይይት የተደረገ ሲሆን በተነሱት ሀሳብና ጥያቄዎች ላይ ከመድረክ ማብራሪያና ምላሽ ተሰጥቷል።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments