ባለስልጣኑ የአዲስ አበባ ወንዞችና የወንዞች ዳርቻ ከብክለት ፀድተው የመዝናኛ ስፍራዎች እንዲሆኑ እየሰራ መሆኑ ገለፀ
ባለስልጣኑ የአዲስ አበባ ወንዞችና የወንዞች ዳርቻ ከብክለት ፀድተው የመዝናኛ ስፍራዎች እንዲሆኑ እየሰራ መሆኑ ገለፀ
06/07/2017 ዓ.ም
****አዲስ አበባ****
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣ ከአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ጋር በመተባበር ወንዞችና የወንዞች ዳርቻ የበከሉ ድርጅቶችና ግለሰቦችን በዛሬው እለትም በደንብ ቁጥር 180/2017 መሰረት 3,669,000 / ሦስት ሚሊየን ስድስት መቶ ስልሳ ዘጠኝ ሺህ/ ብር የገንዘብ ቅጣት በመቅጣት አስተዳደራዊ እርምጃ መውሰዱን አስታወቀ፡፡
ባለስልጣኑ በዛሬው እለት በየካ ክፍለ ከተማ 2,554,000 ብር፣በአራዳ ክፍለ ከተማ 600,000 ብር፣በለሚኩራ ክፍለ ከተማ 450,000ብር ፣በልደታ ክ/ከተማ 50,000 ብር እና በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ 15,000 ብር በመቅጣት ለመንግስት ገቢ ማድረጉን ገልጿል።
በአጠቃላይ በዛሬው እለት ደንብ የተላለፉ 10 ድርጅቶች እና
8 ግለሰቦች በድምሩ 3,669,000 / ሦስት ሚሊየን ስድስት መቶ ስልሳ ዘጠኝ ሺህ/ብር በመቅጣት አስተዳደራዊ እርምጃ ወስዷል።
ባለስልጣኑ የአዲስ አበባ ወንወዞችና የወንዞች ዳርቻ ከብክለት ፀድተው የመዝናኛ ስፍራዎች እስኪሆኑ የግንዛቤና ህግ የማስከበሩ ስራ አጠናክሮ አንደሚቀጥል አስታውቋል።
መረጃው:- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኔኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments