ባለስልጣኑ በዛሬው እለት ደንብ ቁጥር 180/20...

image description
- In code inforcement    0

ባለስልጣኑ በዛሬው እለት ደንብ ቁጥር 180/2017 የተላለፉ ድርጅቶች እና ግለሰቦችን 4,505,000 /አራት ሚሊየን አምስት መቶ አምስት ሺህ/ ብር መቅጣቱ አስታወቀ

ባለስልጣኑ በዛሬው እለት ደንብ ቁጥር 180/2017 የተላለፉ ድርጅቶች እና ግለሰቦችን 4,505,000 /አራት  ሚሊየን አምስት መቶ አምስት ሺህ/ ብር መቅጣቱ አስታወቀ
        
                 07/07/2017 ዓ.ም
             ****አዲስ አበባ****

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣ ከአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ጋር በመተባበር  ወንዞችና የወንዞች ዳርቻ የበከሉ ድርጅቶችና ግለሰቦችን  በዛሬው እለትም በደንብ ቁጥር 180/2017 መሰረት  4,505,000/ አራት  ሚሊየን አምስት መቶ አምስት ሺህ/ ብር የገንዘብ ቅጣት  በመቅጣት  አስተዳደራዊ እርምጃ መውሰዱን አስታወቀ፡፡

ባለስልጣኑ በዛሬው እለት በየካ ክፍለ ከተማ 3,740,000 ብር፤በአራዳ ክፍለ ከተማ 600,000 ብር ፤በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ 165,000ብር ቅጣት ተቀጥቷል።

በአጠቃላይ በዛሬው እለት 10 ድርጅቶች እና
13 ግለሰቦችን በድምሩ 4,505,000 /አራት  ሚሊየን አምስት መቶ አምስት ሺህ/ብር በመቅጣት  አስተዳደራዊ እርምጃ ወስዷል።

ባለስልጣኑ ወንወዞችና የወንዞች ዳርቻ የሚበክሉ ድርጅቶችና ግለሰቦች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ እያሳሰበ ህግ የማስከበሩ ስራ አጠናክሮ  አንደሚቀጥል አስታውቋል።

መረጃው:- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኔኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments