የስልጠናና ቅድመ መከላከል ዘርፍ የስራ አፈጻጸ...

image description
- In code inforcement    0

የስልጠናና ቅድመ መከላከል ዘርፍ የስራ አፈጻጸሙን ገመገመ።

የስልጠናና ቅድመ መከላከል ዘርፍ  የስራ አፈጻጸሙን ገመገመ። 

                08-07 -2017 ዓ.ም
                  አዲስ አበባ 

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን የስልጠናና ቅድመ መከላከል ዘርፍ ከአስራ አንዱንም ክ/ከተማ ከተወጣጡ የቅድመ መከላከልና ስልጠና አስተባባሪዎች ጋር የደንብ ቁጥር 180/2017 አፈፃፀም እና የ3ኛ ሩብ ዓመት የስራ አፈጻጸም ዙሪያ ውይይት አካሂዷል ። 

በመድረኩ ንግግር ያደረጉት የባለስልጣኑ ም/ስራ አስኪያጅ አቶ ንጋቱ ዳኛቸው አንደተናገሩት በከተማችን የሚገኙ የህብረተሰብ አካላት የደንብ ጥሰትን እንዳይፈጽም እና እንዲጸየፍ ለማድረግ እየተሰጡ ያሉ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎችን ማጠናከር አስፈላጊ ነው። 

ተሻሽለው የሚቀርቡትን ደንብ  ፖራ ሚሊተሪ ኦፊሰሩ በቂ እውቀት ኖሮት እና የተሻለ ግንዛቤ በመያዝ ወደ ህብረተሰቡ በማውረድ  ሰፊ ግንዛቤ መፍጠር እንዲቻል በማድረግና ህብረተሰቡ የደንብ ጥሰት መከላከል አላስፈላጊ መሆኑን በማስረዳት በጋራ አብሮን አንዲሰራ ማድረግ አንደሚገባ ም/ስራ አስኪያጁ ገልጸዋል ። 

አክለውም ኦፊሰሮቻችን ስነምግባር የተላበሱ ከሙስናና ብልሹ አሰራር የጸዱ እንዲሆን የተለያዩ ስልጠናዎች እየተሰጡ መሆኑን ተናግረዋል ። 

የመድረኩ ተሳታፊዎች የስራ አፈጻጻም የየክፍለ ከተማቸው ሪፖርት ያቀረቡ ሲሆን ደንብ ቁጥር 180/2017 ከቅጣቱ በፊት ግንዛቤ ላይ ትኩረት ተሰጥቶበት መሠራቱን ገልጸዋል ።

በመጨረሻም ከተሳታፊዎች ጋር ውይይት በማድረግ ለተነሱ ሀሳብና ጥያቄዎች ከመድረኩ ምላሽ ተሰጥቶበት ቀጣይ የስራ አቅጣጫ የባለስልጣኑ ም/ስራ አስኪያጅ አቶ ንጋቱ ዳኛቸው አስቀምጠዋል ። 

ዘገበው ፡-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳሬክቶሬት ነው፡፡


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments