ለስድስተኛ ዙር ፖራ ሚሊተሪ ኦፊሰሮች ስልጠና አ...

image description
- In code inforcement    0

ለስድስተኛ ዙር ፖራ ሚሊተሪ ኦፊሰሮች ስልጠና አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላት የምስጋና፣የእውቅናና ሽልማት ፕሮግራም ተካሄደ

ለስድስተኛ ዙር ፖራ ሚሊተሪ ኦፊሰሮች ስልጠና አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላት የምስጋና፣የእውቅናና ሽልማት ፕሮግራም ተካሄደ

               07-10 -2017 ዓ.ም
                 **** አዲስ አበባ****

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ለስድስተኛ ዙር ፖራ ሚሊተሪ ኦፊሰር ከስልጠና ጀምሮ እስከ ምርቀት ፕሮግራም መሳካት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላት በሳሬም ሆቴል የምስጋና እና እውቅና ፕሮግራም ተካሄደ ። 

በመድረኩ ንግግር ያደረጉት የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ የስድስተኛ ዙር ስልጠና እንዲከናወን ሌት ተቀን በመስራት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላበረከቱ የባለስልጣኑ እና  አጋር ተቋማት ሰራተኞች በተቋሙ ስም ምስጋና አቅርበዋል።

አክለውም  በስራውም ላይ በመተባበር ከተማዋን ከደንብ መተላለፍ የጸዳች ለነዋሪዎቿ እና ለእንግዶች ምቹ ማድረግ ይገባናል ሲሉ ተናግረዋል ። 

የእለቱ የክብር እንግዳ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሊድያ ግርማ ስልጠናው በታሰበለት ግብ ውውጤታማ እንዲሆን ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላበረከታችሁ አካላት  በሰላምና ጸጥታ ስም ምስጋናቸውን አቅርበው የተሰጣችሁ እውቅናና ምስጋና ለቀጣይ ተጨማሪ ኃላፊነትም ጭምር እንዲሆን ለማስታወስ እወዳለሁ ብለዋል።

ከተማችን ከመዘመኗ ጋር አብሮ የዘመነ የጸጥታ ሀይልና ደንብ አስከባሪ ሰራዊት ያስፈልጋታልበዚህ አግባብ የደንብ ስራንም በማጠናከር ፈረቃውን ወደ ሶስት በማድረግ በከተማዋ የሚስተዋሉ የደንብ መተላለፎች ላይ በቁርጠኝነት መከላከል እንደሚገባ ክብርት ወ/ሮ ሊድያ ግርማ አሳስበዋል ። 

ዘገበው ፡-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳሬክቶሬት ነው፡፡


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments