
ባለሥልጣኑ የቀጣይ 90 ቀናት እቅድ በተመለከተ ከማዕከል ሰራተኞች ጋር ውይይት አደረገ
ባለሥልጣኑ የቀጣይ 90 ቀናት እቅድ በተመለከተ ከማዕከል ሰራተኞች ጋር ውይይት አደረገ
ሰኔ 9/2017 ዓ.ም
****አዲስ አበባ****
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን የቀጣይ 90 ቀናት እቅድ በተመለከተ አና በኢትዮ ኮደር የባለስልጣኑ ከማዕከል ሰራተኞች ጋር በባለስልጣኑ መሰብሰቢያ አዳራሽ የውይይት አካሂዷል ።
የባለስልጣኑ ዋና ስራ-አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ በቀጣይ 90 ቀናት በይበልጥ ሰው ተኮር ስራዎች የሚሰሩበት እንደመሆኑ ሁሉም የበኩሉን መወጣት እንደሚገባ እና የኢትዮ ኮደር ስልጠናንም ሁሉም ሰራተኛ ሊተገብር እንደሚገባ ቀጣይ የስራ አቅጣጫ ተሰጥቷል።
የባለስልጣኑ የ90 ቀናት እቅድ በተመለከተ ባለስልጣኑ ምክትል ስራ አስኪያጅ በአቶ ንጋቱ ዳኛቸው አቅርበዋል ።
በዕቅዱ ህገወጥ የንግድ እንቅስቃሴን መከላከል መቆጣጠር ፣ የአረንጓዴ አሻራና የጽዱ ኢትዮጵያ ንቅናቄ በችግኝ ተከላ ፣ቤት እድሳት ፣ማዕድ ማጋራት እንዲሁም የኮሪደር ልማት እና የመሰረት ልማት ጥበቃ ስራዎችን በተሳካ ሁኔታ ሊከናወኑ እንደሚገባ ዕቅዱ በዝርዝር አቀርቧል ።
የባለስልጣኑ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቡድን መሪ በሆኑት በአቶ ሚሊዮን ካሳሁን አማካኝነት ስለ ኢትዮ ኮደር ምንነት፣5ሚሊዮን የኢትዮጵያ ኮደሮች ኢኒሼቲቭ ምንድን ነው፣የፕሮግራሙ አለማ፣ ያሉ ፕሮግራም እና አጠቃቀም አስመለክቶ በዝርዝር አቀርቧል ።
ዘገበው ፡-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳሬክቶሬት ነው፡፡
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments