ባለስልጣኑ ኮሪደር መሠረተ-ልማት ላይ በተሽከርካ...

image description
- In code inforcement    0

ባለስልጣኑ ኮሪደር መሠረተ-ልማት ላይ በተሽከርካሪ ጉዳት አድርሰው በተሰወሩ አሽከርካሪዎች 300 ሺህ ብር መቅጣቱ አስታወቀ

ባለስልጣኑ ኮሪደር መሠረተ-ልማት ላይ በተሽከርካሪ ጉዳት አድርሰው በተሰወሩ  አሽከርካሪዎች 300 ሺህ ብር  መቅጣቱ አስታወቀ
      
           10/10/2017 ዓ.ም
          ****አዲስ አበባ****

የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በትላንትናው እለት በአዲስ አበባ  ከተማ  በተሠራው  የኮሪደር ልማት መሰረተ ልማት የእግረኞች መንገድ ላይ በተሽከርካሪ በመሄድ ደንብ ተላልፈው የተሰወሩ  አሽከርካሪዎች ከአዲስ አበባ ከተማ ትራፊክ ፖሊሶች ጋር በመተባበር በቁጥጥር ስር በማዋል መቅጣቱን አስታወቀ ።

ባለስልጣኑ በቂርቆስ ክፋለ ከተማ  ወረዳ 03 ወሎ ሰፈር አካባቢ ግለሰቦችን በህብረተሰቡ ጥቆማ መሠረት ክትትል በማድረግ 3 አሽከርካሪዎች ከነ ተሽከርካሪአቸው  በቁጥጥር ስር በማዋል እያንዳንዳቸው 100.000 (አንድ መቶ ሺህ ብር )በድምሩ 300,000/ሦስት መቶ ሺህ/ ብር መቀጣቱን ገልጸዋል ። 

ባለስልጣኑ የህብረተሰቡ የጋራ ሀብት የሆኑ የኮርደር ልማትና በሌሎች አካባቢ የማገኙ  መሠረተ ልማቶችን፣ለህዝብ የተሰሩ አረንጓዴ ስፍራዎች እና የወንዝ ዳርቻ ፕሮጀክቶችን ደህንነት በመጠበቅ በሀላፊነት እንዲገለገል መልዕክቱን አስተላልፏል፡፡ 

የአዲስ አበባ ከተማ  ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በከተማዋ ደንብ የሚተላለፉ የግልና የመንግስት ድርጅቶች እና ግለሰቦች ላይ የሚወስደውን እርምጃ አጠናክሮ እንደሚቀጥልም  አስታውቋል ። 

ህብረተሰቡ ለማንኛውም የደንብ መተላለፎች  መረጃ  በ9995 ነፃ የስልክ መስመር ጥቆማ እንዲሰጥ ጥሪውን ያቀርባል። 

መረጃው :- የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments