
ባለስልጣኑ ደንብ የተላለፉ የመንገድ ፅዳት ሰራተኞች መቅጣቱን አስታወቀ
ባለስልጣኑ ደንብ የተላለፉ የመንገድ ፅዳት ሰራተኞች መቅጣቱን አስታወቀ
ሀምሌ 02/2017 ዓ.ም
****የአዲስ አበባ****
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ከመንገድ የጠረጉትን ቆሻሻ በፍሳሽ ማስወገጃ መስመር በመድፋት ደንብ የተላለፉ የመንገድ ፅዳት ሰራተኞች በገንዘብናበመቅጣት በዲሲፕሊን እንዲጠየቁ ማድረጉ አስታወቀ።
ባለስልጣኑ በለሚኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 08 በተለምዶ ሳፋሪ አካባቢ በመንገድ ፅዳት የተመደቡ ሰራተኞች በአካባቢውን መንገድ አፅድተው የሰበሰቡትን ቆሻሻ ቱቦ ውስጥ ሲደፉ ከህብረተሰቡ በደረሰው ጥቆማ መሠረት እያንዳንዳቸው 2 ሺህ ብር በመቅጣት የደፉትን ቆሻሻ እንዲያነሱት ተደርጓል።
ተቋሙ የተወሰደው የቅጣት እርምጃ በከተማው ደንብ የሚተላለፍ የትኛውም የህብረተሰብ ክፍል እኩል ተጠያቂ እንደሚያደረግ ማሳያ መሆኑ ተጠቁሟል።
በከተማው ብርዱና ፀሀዩ ሳይበግራቸው የከተማችንን መንገዶች ፅዳት የሚጠብቁ ጠንካራ ሰራተኞች እያመሰገነ በግዴለሽ ሰራተኞችን በመከታተል አስተማሪ ቅጣት እንደሚወስድ ባለስልጣኑ አሳውቋል።
ህብረተሰቡ ለሠጠን መረጃ እያመሰገንን ለማንኛውም የደንብ መተላለፎች መረጃ በ9995 ነፃ የስልክ መስመር ጥቆማ እንዲሰጥ ባለስልጣኑ ጥሪውን ያቀርባል።
መረጃው፡-የባለሥልጣኑ ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳሬክቶሬት ነው፡፡
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments