የኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ደንብ ማስከበር ጽ/...

image description
- In code inforcement    0

የኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት የደም ልገሳ እና የፎቶ አውደ ርዕይ ፕሮግራም አካሄደ

የኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት የደም ልገሳ እና የፎቶ አውደ ርዕይ ፕሮግራም አካሄደ 

               04- 11- 2017 ዓ.ም
               ****አዲስ አበባ****    

የአዲሰ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት በበጀት አመቱ ለ3ተኛ ዙር የደም ልገሳ ፕሮገራም እና ዓመታዊ ስራዎች በከፊል የሚያሳይ የፎቶ አውደ ርዕይ ፕሮግራም አካሂደዋል ። 

በፕሮግራሙ መክፈቻ ፣ የኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ የብልጽግና ፖርቲ ኃላፊ ሙሉጌታ ጉልማ ፣የደንብ ማስከበር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሙሉጌታ ጎንፋ ፣ የክ/ከተማው የሰላምና ጸጥታ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ያሲን መሀመድ፣ የወረዳ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት ኃላፊዎች፣ ኦፊሰሮች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል ። 

የደንብ ማስከበር ጽ/ቤት በክፍለ ከተማው የሚታዩ የደንብ ጥሰቶችንና ህገወጥ ተግባራት በመከላከል በርካታ ስራዎችን እያከናወነ የሚገኝ ሲሆን በበጀት ዓመቱ ያከናወናቸዉን ስራዎችንም ለህብረተሰቡ ለማሳየት የፎቶ አውደ ርዕይ አዘጋጅቶ ለተመልካች ክፍት ማድረጉ ሊበረታታ የሚገባ ተግባር መሆኑን የኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ የብልጽግና ፖርቲ ኃላፊ ሙሉጌታ ጉልማ ተናግረዋል ። 

በፕሮግራሙ ንግግር ያደረጉት የኮልፌ ቀራንዬ ክ/ከተማ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሙሉጌታ ጎንፋ የፎቶ አውደ ርዕዩ  በ2017 በጀት ዓመት የተከናወኑ መደበኛ ስራዎችና ዋና ዋና ተግባራት ፣  የበጎ ፍቃድና ሰው ተኮር ተግባራት፣  የቅንጅት ስራዎች እንዲሁም በርካታ ተግባራትን የተካተቱበት ሲሆን ማህበረሰቡ እየተመለከተ ሀሳብና አስተያየት እንዲሰጥበት ዝግጅት መደረጉ ገልጸዋል ።

በእለቱ "ደሜን ለወገኔ " በሚል መሪ ቃል በክ/ከተማው የሚገኙ ሰራተኞችን እና ኦፊሰሮችን በማስተባበር የደም ልገሳ ፕሮግራም በበጀት አመቱ  ለ3ኛ ጊዜ የተካሄደ መሆኑ ተገልጿል ። 

መረጃው :- የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments