
ባለስልጣኑ "በመትከል ማንሰራራት! " በሚል መሪ ቃል በችግኝ ተከላ መረሃ-ግብር አስጀመረ
ባለስልጣኑ "በመትከል ማንሰራራት! " በሚል መሪ ቃል በችግኝ ተከላ መረሃ-ግብር አስጀመረ
ሀምሌ 5/2017 ዓ.ም
****አዲስ አበባ****
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባስልጣን ከፍተኛ አመራሮች፣የለሚ ኩራ ፣የጉለሌ እና የቦሌ ክፍለ ከተማና የየካ ክፍለ ከተማ አመራሮች እና ፓራ ሚሊተሪ ኦፊሰሮች በጋር በመሆን የ2017/18 ዓ.ም የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ መርሃ-ግብር ‘’በመትከል ማንሰራራት’’ በሚል መሪ ቃል በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01 ፈረንሳይ ለጋሲዎን አካባቢ በተዘጋጀው ቦታ በመትከል አሻራቸውን አኑረዋል።
የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ እንደተናገሩት ባለስልጣኑ የደንብ ጥሰቶችን ከመከላከልና ከመቆጣጠር ባሻገር የአቅመ ደካማ ቤት በማደስ ፣ ደጋፊ የሌላቸውን ህፃናት በመደገፍ ፣ ደም በመለገስ እና የችግኝ ተከላ በማካሄድ በበጎ ተግባራት በግንባር ቀደም መሳተፋቸው ገልጸዋል።
ሻለቃ ዘሪሁን አያይዘውም የችግኝ ተከላ መርሀ-ግብሩ ለተከታታይ 3 ቀናት እንደሚቀጥል በመግለፅ በከተማው የተጀመረውን የአረንጓዴ ልማት ስራዎችን ለማጠናከር እና ከተማዋን ውብ፣ ፅዱ እና ለነዋሪዎቿ ምቹ ለማድረግ የችግኝ ተከላ መርሃ-ግብር በማካሄድ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ማድረጉ ተናግረዋል፡፡
በየካ ክፍለ ከተማ ውበትና አረንጓዴ ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ መለሰ ከበደ ባለስልጣኑ ሀገራዊ ተልዕኮን በመቀበል ዘንድሮ የሚተከለውን ችግኝ ለመትከል ወደ ክፍለ ከተማችን በማጣቱ በማመስገን በቀጣይ የፅድቀት መጠኑን እንክባካቤ እንደሚያደርግ ከፍተኛ እምነት እንዳላቸው ገልጸዋል።
ባለስልጣኑ ችግኞችን መትከል ብቻ ሳይሆን በአግባቡ እንክብካቤ በማድረግ ከዚህ በፊት ከነበረው በላቀ መንገድ እንዲፀድቅ ለማድረግ በትኩረት እንደሚሰራ የገለፁት የባለስልጣኑ ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ ከፍያለው ታደሰ ናቸው ።
በችግኝ ተከላ መርሐ ግብሩ ከ3000/ከሶስት ሺህ/በላይ ችግኞችን የተተከለ ሲሆን የጥላ፣ የውበት እና የፍራፍሬ ዛፎች እንደሚገኙበት ተገልጿል።
የችግኝ ተካላ መርሃ ግብሩን ያከናወኑት አመራርና ሰራተኞች ችግኙን በመትከል እንደተሳተፉ ሁሉ በቀጣይም በመንከባከብ ለኑሮ ተስማሚ አካባቢን በመፍጠር ለትውልድ ለማስረከብ አሻራችዎን እንደሚያቆዩ ተናግረዋል ።
መረጃው :- የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments