ባለስልጣኑ "በመትከል ማንሰራራት" በሚል መሪ ቃ...

image description
- In code inforcement    0

ባለስልጣኑ "በመትከል ማንሰራራት" በሚል መሪ ቃል የሁለተኛ ዙር የችግኝ ተከላ መርሀ- ግብር አካሄደ

ባለስልጣኑ "በመትከል ማንሰራራት" በሚል መሪ ቃል የሁለተኛ ዙር የችግኝ ተከላ መርሀ- ግብር አካሄደ

            ሐምሌ 06/2017 ዓ.ም
          ****አዲስ አበባ****

የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በትላንናው እለት የተጀመረው የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ከአቃቂ ቃሊቲ፣ ከንፋስ ስልክ ላፍቶ፣ ከኮልፌ ቀራኒዮ እና ከአዲስ ከተማ ክ/ከተሞች አመራሮች እና ኦፊሰሮች ጋር በመሆን በዛሬው እለትም አከናወነ ።

በመርሀ ግብሩ ላይ የተገኙት የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘርይሁን ተፈራ የ2017 አረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር " በመትከል ማንሰራራት" በሚል መሪቃል በመጀመር በክቡር ጠቅላይ ሚስቴር በመቀጠልም በክብርት ከንቲባች ወ/ሮ አዳነች አበቤ በይፋ መጀመሩን ተከትሎ ተቋሙም ይህን ተግባር በመቀበል የዛሬው ለሁለተኛ ዙር መሆኑ ገልፀዋል።

ዋና-ስራ አስኪያጁ  ለቀጣዩ ትውልድ ንፁህ አየር እና አካባቢ ለማስረከብ አብዝተን እንተክላለን የተከልነውን እንንከባከባለን ብለዋል። 

ባለስልጣኑ በቀጣይ በክረምት በጎ ፈቃድ ተግባሮቻችን የአቅመ ደካሞች ቤት ማደስ፣ የማእድ ማጋራት እና የደም ልገሳ መርሀ ግብሮችን እንደሚካሄድ ተመላክቷል።

 በመርሀ ግብሩ ላይ የባለስልጣኑ ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም  የአቃቂ ቃልቲ፣ የንፋስ ስልክ ላፍቶ፣ የኮልፌ እና የአዲስ ከተማ ክ/ከተሞች አመራሮች እና ሰራቸኞች ተገኝተዋል። 

በእለቱ ከችግኝ ተከላ ፕሮግራም በኋላ አብሮነትን ለማጠናከር በክፍለ ከተማ ኦፊሰሮች መካከል የገመድ ጉተታ ስፖርታዊ ውድድር ተካሂዷል።

በውድድሩ አዲስ ከተማ ከኮልፌ ቀራንዮ  ክፍለ ከተማ ያደረጉት ውድድር አዲስ ከተማ በሁለቱም ጾታውድድር ሲያሸንፍ በአቃቂ ቃልቲ እና በነፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ የተካሄደው ውድድር አቃቂ ቃሊቲ በሴቶች ውድድር ሲያሸንፍ ንፋስ ስልክ ላፍቶ በወንዶች አሸንፏል።

የችግኝ ተከላ መርሀ-ግብር በነገው እለትም ከሌሎች ክፍለከተሞች ጋር በጋራ  እንደሚቀጥል ተመላክቷል።

ዘገባው:- የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments