
ከ1100 በላይ የሚሆኑ የባለስልጣኑ የአመራሮችና ሰራተኞች የደም ልገሳ አደረጉ
ከ1100 በላይ የሚሆኑ የባለስልጣኑ የአመራሮችና ሰራተኞች የደም ልገሳ አደረጉ
ሐምሌ 11- 2017 ዓ.ም
****አዲስ አበባ****
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ከአዲስ አበባ ከተማ የኅብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፍቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን ጋር በመተባበር "ደም መስጠት ህይወት መስጠት ነው " በሚል መሪ ቃል የደም ልገሳ መርሐ ግብር በአበበ ቢቂላ ስታዲየም አከናወነ።
የባለስልጣኑ ዋና ሰራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ በክረምት በጎ ፍቃድ ከዘጠና ቀናት እቅድ አንዱ የሆነውን የደም የመለገስ መርሃ-ግብር አመራሩና ኦፍሰሩ በጋራ በመሆን በራስ ተነሳሽነት ደም ለመስጠት መገኘቱ የህሊና እርካታ የሚሰጥና ደም በመስጠት ክቡር የሆነውን የሰው ልጅ ህይወት ለመታደግ መሆኑ ተናግረዋል።
አክለውም ደም ልገሳ የሁሉንም ህብረተሰብ ክፍሎች ተሳትፎ የሚጠይቅ ታላቅ ሰብዓዊ አገልግሎት ሱሆን በተለያየ ምክንያትና አደጋ በደም እጦት የሚሞቱ ወገኖቻችንን ደም በመስጠት ህይወት የማዳን ስራ ለመስራት የበኩላችንን ልንወጣ ይገባል ብለዋል፡፡
በመርሐ ግብሩ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኅብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፍቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ይመር ከበደ ከስጦታዎች ሁሉ ዉዱ ስጦታ የሆነውን የሰውን ልጅ ህይወት የሚያድነውን ደም ለመለገስ ፍቃደኛ ሆነው የተገኙ ከ1100 በላይ የሚሆኑ የደንብ ማስከበር አመራሮችና ኦፊሰሮች ከፍተኛ ምስጋና ይገባቸዋል ሱሉ ተናግረዋል ።
በቀጣይም በቋሚነት አባል ሆነን በየሶስት ወሩ ደም በመለገስ ኃላፊነታችንን ልንወጣ ይገባል ሲሉ የኮሚሽኑ ኮሚሽነር አቶ ይመር ከበደ መልዕክት አስተላልፈዋል ።
በደም ልገሳ መርሐ ግብር የባለስልጣኑ የክፍለ ከተማና የወረዳ ጽ/ቤት አመራሮች፣ የማዕከል ሰራተኞች፣ከ11 ክፍለ ከተማ እና ከ119 ወረዳዎች በጎ-ፈቃደኛ ደም ለጋሽ ኦፊሰሮች ተሳትፈዋል ።
በመርሀ ግብሩ ባለስልጣኑ በከተማዋ የደንብ መተላለፎች ከመከላከልና ከመቆጣጠር በተጨማሪ በርካታ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ላይ በመሳተፍ የሀገር አለኝታ መሆኑ ተገልጿል።
መረጃው :- የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments