ባለስልጣኑ ከሰላምና ፀጥታና ከንግድቢሮ አመራሮች...

image description
- In code inforcement    0

ባለስልጣኑ ከሰላምና ፀጥታና ከንግድቢሮ አመራሮች ጋር በመሆን የምሽት የንግድ እንቅስቃሴ የመስክ ምልከታ አደረገ

ባለስልጣኑ ከሰላምና ፀጥታና ከንግድቢሮ አመራሮች ጋር በመሆን የምሽት የንግድ እንቅስቃሴ የመስክ ምልከታ አደረገ

               ሐምሌ 15/2017 ዓ.ም
               *****የአዲስ አበባ ****

የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ከሰላምና ፀጥታና ከንግድቢሮ አመራሮች ጋር በመሆን የምሽት የንግድ እንቅስቃሴ የመስክ ምልከታ በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ የንግድ ተቋማት የምሽት  ግብይት የወጣውን ደንብ ተግባራዊ መደረጉን የመስክ ምልከታ አካሄደ።

በጉብኝቱ የአዲስ አበባ ከተማ የሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ሀላፊ በወ/ሮ ሊዲያ ግርማ፣በንግድ ቢሮ ሀላፊ በወ /ሮ ሀቢባ ሲራጅ እና የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ እና ሌሎች የክፍለ ከተማውና የወረዳ አመራሮች ተገኝተዋል፡፡ 

በምልከታውም  የከተማውና የክፍለ ከተማው የህገወጥ ንግድ ቁጥጥር የገበያ ማረጋጋት ግብረ ኃይል አባላትም ተገኝተዋል፡፡

የጉብኝቱ  ዓላማ  የንግድ ተቋማት በተቀመጠላቸው የሥራ ሰዓት ገደብ ክፍት ሆነው በአገልግሎት ላይ መሆናቸውንናየወጣውን ደንብ ተግባራዊ መሆኑን ለማረጋገጥ እንደሆነ ተጠቅሷል።

በጉብኝቱም የተቋማት የምሽት ንግድ እንቅስቃሴ የከተማዋን ፈጣን ዕድገት ተከትሎ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ እንቅስቃሴን ይበልጥ እንደሚያሳድግ ተብራርቷል። 

የምሽት ንግድ አገልግሎት መስፋፋት የከተማዋን የንግድ እንቅስቃሴ በማነቃቃት የዜጎችን ገቢ ከፍ ከማድረግ ባለፈ ለተጨማሪ የሥራ ዕድሎች መፈጠርና የስራ ባህልን እንደሚያሳድግም ተመላክቷል። 

በምልከታው የክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ኒእመተላህ ከበደ የተገኙ ሲሆን በክፍለ ከተማው የተቋማት የምሽት የስራ ሰዓት ገደብ አተገባበርን አስመልክቶ  ለግብረ ሀይል አባላት ገለፃ አድርገዋል።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments