ባለስልጣኑ እስከ ምሽቱ አራት ስዓት ህገ-ወጥ የ...

image description
- In code inforcement    0

ባለስልጣኑ እስከ ምሽቱ አራት ስዓት ህገ-ወጥ የንግድ እንቅስቃሴዎች በመቆጣጠር ሰላማዊ ግብይት እንዲኖር እየሰራ መሆኑ ተገለፀ

ባለስልጣኑ እስከ ምሽቱ አራት ስዓት ህገ-ወጥ የንግድ እንቅስቃሴዎች በመቆጣጠር ሰላማዊ ግብይት እንዲኖር እየሰራ መሆኑ ተገለፀ

            ሐምሌ 16/2017 ዓ.ም
              ****አዲስ አበባ**** 

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ከሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ እና ከንግድ ቢሮ ጋር በጋራ በመሆን በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ የንግድ ተቋማት የምሽት ንግድ ስራዎችና ግብይት ላይ የወጣውን ደንብ ተግባራዊ መደረጉን የመስክ ምልከታ አካሂደዋል። 

የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ የስራ ባህልን እንደ ሀገር ለማሳደግ የንግድ ሱቆች ስራዎች በምሽት እየሰሩ የሚገኙ ሲሆን አንዳንድ የደንብ ጥሰቶችና ህገወጥ እንቅስቃሴዎች ለመከላከል ደንብ ማስከበር ሽፍቱን አጥፎ እስከ ምሽቱ አራት ስዓት በመስራት የህገወጥ ንግድ ቁጥጥርና የገበያ ማረጋጋት ስራዎችን ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን እየሰራ እንደሚገኝ ገልፀዋል ። 

በከተማችን የሚገኙ የንግድ ሱቆች እስከ ምሽት 4:00 ሰዓት እየሰሩ እንደሚገኙ በተደረገው ምልከታ ሰላማዊ የሆነና ምንም አይነት የጸጥታ ችግር ሳይኖር የንግድ እንቅሰቃሴው በመልካም ሁኔታ እየተካሄደ እንደሚገኝ በምልከታው ተረጋግጧል።

በምልከታው በአንዳንድ አካባቢዎችዎ ይታያሉ ተብለው ከነጋዴዎች የተሰጡ የትራንስፖርት ችግር አስተያየቶችን ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በመነጋገር መፍትሔ እንዲሰጥና እንደሚስተካከል የአዲስ አበባ ከተማ የሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሊድያ ግርማ ተናግረዋል ። 

አክለውም ምሽት ላይ የጸጥታ ችግር ይኖራል የሚል ስጋት እንዳይኖር በ7/24 የስራ ባህል የጸጥታ መዋቅሩ ከተማዋን እየጠበቀ የሚገኝ ሲሆን የምሽት ንግድ እንቅስቃሴ የከተማዋን ፈጣን ዕድገት ተከትሎ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ እንቅስቃሴን ይበልጥ አንደሚያሳድግ ገልጸዋል ። 

የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ እንደተናገሩት ከተማችን ሶስተኛ የዲፕሎማሲ መቀመጫና ትልቅ ከተማ እንደመሆኗ የምሽት ንግድ መኖሩ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴው ላይ መነቃቃት የሚፈጥርና የስራ ባህልን የሚያሳድግ ነው። 

በምልከታውም የባለስልጣኑ፣የሰላምና ጸጥታና የንግድ ቢሮ የከተማውና የክፍለ ከተማው አመራሮች ፣ የኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ፣ኦፊሰሮችና የሰላም ሰራዊት አባላት ተገኝተዋል ፡፡ 

መረጃው:- የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments