
በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ የምሽት የንግድ ተቋማት ሰላማዊ ግብይት እየተካሄደ እንደሚገኝ ተገለፀ
በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ የምሽት የንግድ ተቋማት ሰላማዊ ግብይት እየተካሄደ እንደሚገኝ ተገለፀ
16- 11- 2017 ዓ.ም
****አዲስ አበባ****
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ከከተማው ንግድ ቢሮ ጋር በመሆን በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ የንግድ ተቋማት የምሽት ስራዎች እንቅስቃሴ ምልከታ አካሂደዋል።
የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ በምሽት የንግድ እንቅስቃሴ ወቅት የደንብ ጥሰት እንዳይኖር የምሽት ምድብ በመመደብ እየተሰራ መሆኑን ጠቁመው እስካሁን የምሽት ስራው የሚያስተጓጉል የደንብ ጥሰትና የፀጥታ ችግር እንዳላጋጠመ ገልፀዋል።
የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ እንደተናገሩት ከተማችን አዲስ አበባ የአፍሪካ ህብረትና የበርካታ ሃገራት ኢምባሲዎች መቀመጫ እንደመሆኗ መጠን ይህንን የሚመጥን የምሽት ንግድ እንቅስቃሴ እንዲኖራት እየተሰራ መሆኑን ገልፀው ይህም በከተማዋን አጠቃላይ የኢኮኖሚ ዘርፍ ይበልጥ የሚያነቃቃ ነው ብለዋል።
የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አድማሱ ደቻሳ በበኩላቸው በክፍለ ከተማው የምሽት የንግድ እንቅስቃሴ ፍፁም ሰላማዊ በሆነ መንገድ እየተካሄደ መሆኑን ጠቅሰው የፀጥታ ችግር እንዳይኖር ህብረተሰቡን በባለቤትነት በማሳትፍ እየተሰራ እንደሚገኝ ገልፀዋል። ዋና ስራ አስፈፃሚው አክለው የምሽት ግብይት ለንግዱ ማህበረሰብ እና በትራንስፖርት ለተሰማሩት ከሚያበረክተው ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ በተጨማሪ ማህበራዊ መስተጋብር ከማሳደግ አንፃር ትልቅ ሚና አለው ብለዋል።
በተለያዩ ጊዜያት በሰራው የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራ በክፍለ ከተማው የሚገኙ የንግድ ተቋማት እስከ ምሽቱ 4 ሰዓት ድረስ አገልግሎት እየሰጡ መሆኑን አቶ አድማሱ ገልፀው የክፍለ ከተማው ነዋሪዎችም ያለምንም ስጋት እንዲገበያዩ ጠይቀዋል።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments