
በመትከል ማንሰራራት" በሚል መሪ ቃል 7ኛዉ የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሐ-ግብር ተካሂደ
"በመትከል ማንሰራራት" በሚል መሪ ቃል 7ኛዉ የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሐ-ግብር ተካሂደ
ሐምሌ 22/2017ዓ.ም
*******
በአዲስ አበባ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ"በመትከል ማንሰራራት" በሚል መሪ ቃል 7ኛዉ የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሐ-ግብር ተካሂዷል።
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ሃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሊድያ ግርማ በመርሃ ግብሩ ላይ በመገኘት ባደረጉት ንግግር
በከተማችን 6 ሚሊዮን ችግኞች ተክለናል ያሉት ኃላፊዋ ተክሎ መሄድ ብቻ ሳይሆን በመንከባከብ ለሚፈለገው ግብ ማድረስ ይገባል ሲሉ አሳስበዋል። የችግኞችን ማጽደቅ ደረጃ 75% ማድረስ ማቻሉን ገልፀው ዛሬም የከተማችንን የፀጥታ መዋቅርና የተለያዩ አደረጃጀቶችን በማስተባበር 25,000 ችግኞች እንተክላለን ብለዋል።
ከተማችን አዲስ አበባ እንደስሟ ውብ ለማድረግ ሰላም በመጠበቅ ብቻ ሳይሆን በአረንጓዴ አሻራም ለማስዋብ ትልቁን አስተዋጽኦ ማድረጋቸውን ጠቁመው አሁንም የከተማችን ዘላቂ ሰላም ለማረጋገጥ ተግተን እንሰራለን በማለት ገልፀዋል።
በመርሃ ግብሩ ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት አቶ ግርማ ሰይፍ የአዲስ አበባ ከተማ ውበትና አረንጓዴ ልማት ቢሮ ሀላፊ እንዳሉት ሐምሌ 24 /2017ዓ.ም እንደ ሀገር አቀፍ ከሚደረገው የችግኝ ተከላ መርሐ -ግብር ላይ ከፍተኛ እንቅስቃሴ የተደረገበት መሆኑን አውስተው ለሀገር ሰላም በጋራ የምትተጉ የሰላማችን አለኝታ የሆናችሁ የፀጥታ ኃይሎች ዛሬ ከተማችንን ውብና ዕዱ ለማድረግና አሻራችሁን ለማሳረፍ እዚህ ስለተገኛችሁ ምስጋና ይገባችኋል ብለዋለል።
በመርሐ ግብሩ ላይ ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ሀላፊ፣የአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ ጠ/መምሪያ ዋና አዛዥ፣የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራና
የቢሮው ከፍተኛ አመራሮች፣የኢፊድሪየመከላከያ ሰራዊት አባላት፣የፌደራልና የአዲስ አበባ ፖሊስ አባላት፣የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ከፍተኛ አመራሮችና ኦፊሰሮች፣
የሀይማኖት አባቶች የሰላም ሰራዊት አባላትና በርካታ የህብረተሰብ ክፍሎች ተሳትፈዋል ።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments