
ባለለስልጣኑ በአንድ ጀምበር 700 ሚሊዮን ችግኝ የመትከል መርሀ ግብር አካሄደ
ባለለስልጣኑ በአንድ ጀምበር 700 ሚሊዮን ችግኝ የመትከል መርሀ ግብር አካሄደ
ሐምሌ 24/2017 ዓ.ም
**** አደስ አበባ****
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የአመራሮችና ሰራተኞች በየካና በኮልፌ ክ/ከተማ በአንድ ጀምበር 700 ሚሊዮን ችግኞች መትከል በሚል በሃገር አቀፍ ደረጃ የተያዘውን የ7ኛ ዙር የችግኝ ተከላ መርሀ ግብር አካሂድዋል።
የባለስልጣኑ ምክትል ስ/አስኪያጅ እና የክትትል ቁጥጥርና እርምጃ አወሳሰድ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ከፍያለው ታደሰ በመርሀ ግብሩ ማስጀመሪያ ላይ እያስመዘገበ የመጣውን አመርቂ የሆነ ውጤት ወደፊት ከሚያስቀጥሉ ተግባራት መካከል በሃገር አቀፍ ደረጃ የተያዘውን በአንድ ጀመበር 700 ሚሊዮን ችግኞች የመትከል መርሀ ግብር ከማሳካት አንጻር ችግኞችን ተገቢውን ጥንቃቄ በማድረገ መትከል እና መንከባከብ እንደሚገባ በመጥቀስ የችግኝ ተከላውን አስጀምረዋል።
“በመትከል ማንሰራራት” በሚል መሪ ቃል በተዘጋጀው የችግኝ ተከላ መርሀ ግብር ከፍተኛ አመራሮች፣ የተቋሙ ሰራተኞች፣ የክፍለ ከተማ ኃላፊዎች፣ ኦፊሰሮችን እንዲሁም በአጠቃላይ የበጎ ፈቃድ ሰራዊት እና የአካባቢው ነዋሪዎች በመገኘት አረንጓዴ አሻራቸውን አሳርፈዋል።
በመርሀ ግብሩ ማጠቃለያ ላይ የባለስልጣኑ የጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ተስፋሁን አሉላ ባስተላለፉት መልክት ባለሰልጣኑ እያደረገ የሚገኘውን የበጎ ተግባራትን በማስቀጠል ከዚ በበለጠ ስራዎችን አጠናክሮ መስራት እንደሚገባ በመግለጽ በዛሬው እለትም የተተከሉትን ችግኞች የመንከባከብ እንዲጸድቅ የማድረግ ተግባሩ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ አሳስበዋል።
መረጃው :- የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments