
የባለስልጣኑ አመራሮችና ሰራተኞች "በመትከል ማንሰራራት!" በሚል መሪ ቃል ከ17 ሺህ በላይ ችግኞች በመትከል አረንጓዴ አሻራቸውን አስቀመጡ
የባለስልጣኑ አመራሮችና ሰራተኞች "በመትከል ማንሰራራት!" በሚል መሪ ቃል ከ17 ሺህ በላይ ችግኞች በመትከል አረንጓዴ አሻራቸውን አስቀመጡ
ሀምሌ 24/2017 ዓ.ም
**** አዲስ አበባ****
የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የማዕከል አመራሮችና ሰራተኞች ፣ የ11ዱም ክፍለ ከተማ ጽ/ቤት ኃላፊዎች እና ፓራ ሚሊተሪ ኦፊሰሮች "በመትከል ማንሰራራት!" በሚል መሪ ቃል 700 ሚሊየን ችግኝ በእንድ ጀምበር በመተክል መርሀ ግብር በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01 ፈረንሳይ ለጋሲዎን አካባቢ በሚገኘው ሰፊ ቦታ 16 ሺህ ችግኞችን ለመትከል ተቅዶ 17ሺ 500 በመትከል አሻራቸውን አስቀምጧል ።
የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ በሀገራ አቀፍ ደረጃ በአንድ ጀንበር 700 ሚሊየን ችግኝ የመትከላ መርሀ ግብር ለከተማችን ብሎም ለሀገራችን የአረንጓዴ ሽፋን ለመጨመር በዛሬው ቀን 17 ሺህ 500 ችግኞችን በመትከል አሻራውን እንዳስቀመጠ ገልፀዋል ።
አያይዘውም የባለስልጣኑ ፓራ ሚሊተሪ ኦፊሰሮች የከተማውን ደንብ ጥሰቶች ከመከላከልና ከመቆጣጠር ባሻገር የአቅመ ደካማ ቤት በማደስ ፣ ደጋፊ የላቸውን ህፃናት በመደገፍ ፣ ደም በመለገስ በጎ ተግባራትን እንደሚያከናውን እና በዛሬው ቀንም የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብርን አረንጎዴ በመልበስ አሻራቸውን እንዳስቀመጡ ገልጸዋል።
የባለስልጣኑ ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ ንጋቱ ዳኛቸው ኢትዮጵያን አረንጓዴ የማልበስ መርሃ-ግብር በማስተግበር ባለስልጣኑ ችግኞችን መትከል ብቻ ሳይሆን በአግባቡ እንክብካቤ በማድረግ ከዚህ በፊት ከነበረው በላቀ መንገድ እንዲፀድቅ ለማድረግ በትኩረት እንደሚሰራ ተናግረዋል፡፡
በየካ ክፍለ ከተማ ደንብ መስከበር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ደሳለኝ ከሴ ዘንድሮ የተተከለው ችግኝ በየካ ክፍለ ከተማ እንደመሆኑ በቀጣይ የፅድቀት መጠኑን እንክባካቤ በማድረግ ከፍተኛ አሰተዋፆ እንደሚያደርጉ ተናግረዋል።
የችግኝ ተካላ መርሃ ግብሩን ያከናወኑት አመራር እና ሰራተኞች ችግኙን በመትከል እንደተሳተፉ ሁሉ በቀጣይም በመንከባከብ ለኑሮ ተስማሚ አካባቢን በመፍጠር ለትውልድ ለማስረከብ አሻራችዎን እንደሚያቆዩ ተናግረዋል ።
መረጃው፦ የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments