ሰፊ የግንዛቤ ማስጨበጥ ስራዎች በመስራት የደንብ...

image description
- In code inforcement    0

ሰፊ የግንዛቤ ማስጨበጥ ስራዎች በመስራት የደንብ ጥሰት የመቀነስ ተግባራት በትኩረት እንደሚሰራ ተገለፀ

ሰፊ የግንዛቤ ማስጨበጥ ስራዎች በመስራት የደንብ ጥሰት የመቀነስ ተግባራት በትኩረት እንደሚሰራ  ተገለፀ
             
ነሐሴ  22/2017 ዓ.ም
አ አ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የስልጠና ቅድመ መከላከል ዘርፍ በ2018 በጀት ዓመት ለህብረተሰቡ ሁሉን አቀፍና ሰፊ የግንዛቤ ማስጨበጥ ስራዎች በመስራት የደንብ ጥሰትን የመቀነስ ተግባራት በትኩረት እንደሚሰራ  ገለፀ።
             
ዘርፉ ከክፍለ ከተማ የስራ አስተባባሪዎች እና ቡድን መሪዎች ጋር የ2018 በጀት ዓመት በሚከናወኑ የግንዛቤ ማስጨበጥና የስልጠና ስራዎች እቅድ ውይይት አካሂዷል ።

በመድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የባለስልጣኑ ም/ስራ አስኪያጅ አቶ ንጋቱ ዳኛቸው የከተማዋ ህብረተሰብ ባለማወቅ የደንብ ጥሰት እንዳይፈጽም የግንዛቤ ማስጨበጥ ስራወችን አጠናክሮ በመስራት ደንብ ጥሰት እርምጃ ከመወሰዱ በፊት አስቀድሞ መከላከል እንደሚገባ ገልጸዋል ።

አክለውም በበጀት አመቱ ሰፊ የግንዛቤ ማስጨበጥ ስራዎች በመስራት የደንብ ጥሰት የመቀነስ ተግባራት በትኩረት እንደሚሰራና  የደንብ ጥሰትን የሚጸየፍና የኦፊሰሮች አጋዥ የሚሆን ህብረተሰብ ለመፍጠር እንደሚሰራ ገልጸዋል ።

በእለቱ የ2018 በጀት ዓመት እቅድ እና የሀምሌ ወር የግንዛቤ ፈጠራ ስራ የክፍለ ከተሞች አፈጻጸም ሪፖርት በባለስልጣኑ የቅድመ መከላከልና ግንዛቤ ማስጨበጥ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ ስርካለም ጌታሁን ቀርቧል ።

በውይይት ማጠቃለያ የስልጠና ቅድመ መከላከል ዘርፍ ኃላፊ ከ11ክፍለ ከተሞች የደንብ ማስከበር  ጽ/ቤት የቅድመ መከላከል  ስራ አስተባባሪዎች ጋር የ2018 በጀት ዓመት የካስኬዲንግ ዕቅድን ተፈራርመዋል፡፡

መረጃው:- የአዲስ አበባ  ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments