በእግረኞች መንገድ በተሽከርካሪ በመሄድ ደንብ የተላለፈው ግለሰብ እና ወንዝን የበከለ ድርጅት መቀጣቱ አስታወቀ
በእግረኞች መንገድ በተሽከርካሪ በመሄድ ደንብ የተላለፈው ግለሰብ እና ወንዝን የበከለ ድርጅት መቀጣቱ አስታወቀ
29/01/2018 ዓ.ም
** አዲስ አበባ**
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በንፋስ ስልክ ላፍቶ በልማት ኮሪደር በተሰራው እግረኞች መንገድ ላይ በመኪና በመሄድ ደንብ ተላልፎ የተሰወረን አሽከርካሪ ከአዲስ አበባ ትራፊክ ፖሊስ ጋር በመተባበር በቁጥጥር ስር በማዋል 5ዐ,000( ሀምሳ ሺህ ) ብር መቅጣቱን አስታወቀ ።
በተያያዘ ዜና የኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ደንብ ማስከበር ፅ/ ቤት በወረዳ 5 ልዪ ቦታ ዘነበ ወርቅ አደባባይ ኤስ አይ ኤም የተባለ ግብረ ሰናይ/NGO/ድርጅት ፍሳሽ ቆሻሻ ወደ አስፖልት እና ወንዝ በመልቀቅ 300,000ብር(ሶስት መቶ ሺ) ብር በመቅጣት አስተዳደራዊ እርምጃ ተወስዷል።
ህብረተሰቡ በከተማዋ ውስጥ በመንግስትና በህዝብ ሀብት የተገነቡ የኮሪደርና የወንዝ ዳርቻ መሠረተ ልማቶችን ደህንነት በመጠበቅ መገልገልና መጠቀም እንደሚገባ አስታውቋል ፡፡
ባለስልጣኑ ህብረተሰቡ ለማንኛውም የደንብ መተላለፎች መረጃ በ9995 ነፃ የስልክ መስመር ጥቆማ እንዲሰጥ ጥሪውን ያቀርባል።
መረጃው ፡-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳሬክቶሬት ነው፡፡
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments